
የ Anthropic ዋና ስራ አስፈጻሚ Dario Amodei: “የ AI ሞዴሎች ወደ ሰው ልጅ የማሰብ ችሎታ እየተጠጉ ነው: ነገር ግን ህብረተሰቡ በመምጣት ላይ ያለውን አደጋ በደንብ እያወቀው አይደለም”
ጤና ይስጥልኝ የቴክኖሎጂ አፍቃሪያን! ዛሬ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አለም ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት የ Anthropic ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ Dario Amodei የተሰማ እጅግ አሳሳቢ እና ትኩረት የሚሻ መልዕክት ይዘንላችሁ ቀርበናል።
በዚህ ቃለ መጠይቅ ላይ Dario Amodei የAI እድገት አሁን የደረሰበትን ደረጃ እና ወደፊት ሊከተሉ የሚችሉትን ስጋቶች በሚከተለው መልኩ አብራርቷል።
follow us on telegram
Join our Telegram Channelበቅርብ ርቀት ላይ ያለ “ሱናሚ”
Dario Amodeiአሁን ያለውን የ AI እድገት በአድማስ ላይ ከሚታይ ትልቅ ሱናሚ ጋር ያመሳስለዋል። ሱናሚው በግልጽ እየታየ ቢሆንም፣ ብዙ ሰዎች ግን አሁንም ሁኔታውን አምኖ ለመቀበል ፍቃደኛ አይደሉም።
እንደ እርሱ አባባል፣ ሰዎች አደጋውን ከማየት ይልቅ ይህ ሱናሚ አይደለም፤ የብርሃን ነጸብራቅ ነው።
ወይም ሌላ ተራ ክስተት ነው።
የሚሉ ምክንያቶችን በመደርደር ራሳቸውን እያታለሉ ይገኛሉ።
ወደ ሰው ልጅ የማሰብ ደረጃ መቃረብ
የ AI ሞዴሎች አሁን ላይ የሰው ልጅን የማሰብ እና የመተንተን ችሎታ ለመድረስ እጅግ በጣም ጥቂት እርምጃዎች ብቻ ነው የቀራቸው። ይህ እድገት እጅግ ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ ህብረተሰቡ ለውጡን ለመቀበል ዝግጁ አይደለም።
ይህ የብቃት ደረጃ ላይ መድረስ ትልቅ እድል ቢሆንም፣ በቂ ጥንቃቄ ካልተደረገ ግን ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን እንደሚችል Dario Amodei በአጽንኦት ገልጿል።
የመንግስታት እና የህዝብ ግንዛቤ ማነስ
ሌላው እጅግ አሳሳቢው ጉዳይ የህዝብ ግንዛቤ ማነስ ነው። ህብረተሰቡ ሊመጣ ስላለው አደጋ በቂ እውቀት ስለሌለው፣ በመንግስታት ላይ የሚደረገው ጫና አነስተኛ ነው። በዚህም ምክንያት መንግስታት ቴክኖሎጂውን ለመቆጣጠር እና ደህንነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ህጎችን ለማውጣት ዘግይተዋል።
በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂውን ያለ ምንም ገደብ በከፍተኛ ፍጥነት ለማሳደግ የሚጥሩ አካላት ቢኖሩም፣ ይህ ፍጥነት ግን ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋዎች በሚገባ ያጤነ አይደለም።
Dario Amodeiእንደሚለው፣ የቴክኖሎጂውን ጥቅሞች በሚገባ ይገነዘባል: ነገር ግን ከጥቅሙ ጎን ለጎን ሊመጡ የሚችሉትን አደጋዎች በሚገባ መረዳት እና ለደህንነቱ ቅድሚያ መስጠት የወቅቱ ዋና ተግባር ሊሆን ይገባል።
ይህ የAnthropic የስራ አስፈጻሚው መልዕክት ሁላችንም ስለ AI የምናስብበትን መንገድ እንድንመረምር እና ለወደፊቱ ዝግጁ እንድንሆን የሚጋብዝ ነው።
የDario Amodeiን አጭር መልእክት በቀጣዩ ቪዲዮ ይመልከቱ።
Leave a Reply