በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ G Tech Ethiopia አዲስ ነገር ፖስት ስናደርግ ማስታወቂያ እንዲደርስዎት ይፈልጋሉ? አዎ፣ እፈልጋለሁ አይ፣ አመሰግናለሁ።

G Tech Ethiopia – Blog

Free Accessible Video and Audio Editor: Sound and Video

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች!

ዛሬ የቪዲዮ እና የድምጽ ፋይሎችን በቀላሉ ኤዲት ለማድረግ የሚያስችላቹህን ሶፍትዌር እናስተዋውቃቹሃለን።

የሶፍትዌሩ ስም “SoundAndVideo” ይባላል። ይህ ሶፍትዌር ለScreen readers ምቹ ተደርጎ የተሰራ ነው።

ይህንን ጽሁፍ በጥንቃቄ በማንበብ፣ ሶፍትዌሩን ተጠቅሞ ያለምንም ችግር ቪዲዮን ኤዲት ለማድረግ የሚያስችላቹህን እውቀት ታገኛላቹህ።

follow us on telegram

Join our Telegram Channel

Download Sound and Video

Sound and Video የተባለውን ሶፍትዌር ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ

አጠቃላይ ስለ Sound and Video መረጃ

Sound and Video ስክሪን ሪደር ለሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጀ ተደራሽ የቪዲዮ እና የኦዲዮ ኤዲት ማድረጊያ ሶፍትዌር ነው። ይህ መተግበሪያ የሚዲያ ፋይሎችን ሙሉ በሙሉ በ keyboard shortcuts እና menus በመጠቀም መቁረጥ፣ መቀጠል እና ማስተካከል ያስችላል። እያንዳንዱ ተግባር በድምጽ እና በጽሁፍ Feedback የሚረጋገጥ በመሆኑ ያለ ምንም ግምት በሙሉ እውቂያ ይከናወናል።

Features of Sound and Video

Edit menus

in and out markers በመጠቀም ክፍሎችን መቁረጥ፣ copy ማድረግ፣ paste ማድረግ እና merge ማድረግ ይቻላል።

Audio Effects

noise and echo removal, normalization, click removal, bass boost, fades, speed change, እና silence detection or removal የመሳሰሉ አማራጮችን አካቷል።

Video Effects

brightness/contrast fix, black bar cropping, rotation, stabilization, እና auto-orientation ማስተካከያዎችን ይዟል።

More editing options

background images, text overlays, subtitles (SRT, ASS, SSA, VTT), እና mixed-in audio tracks መጨመር ይቻላል።

Bookmarks

ከፋይሉ ጋር አብረው የሚቆዩ bookmarks እና error markers ለቀጣይ ስራዎች ትልቅ እገዛ አላቸው።

themes and Languages

Light theme ወይም dark theme መምረጥ ይቻላል፤ እንዲሁም display language menu ውስጥ English, German, እና Serbian ቋንቋዎች አሉ።

መተግበሪያው MP4, MKV, AVI, MOV, VOB, MP3, WAV, FLAC, OGG, AAC, እና M4A ፋይሎችን በብቃት ይደግፋል። እንዲሁም፣ በ FFmpeg የተደገፈ ነው።

እንዴት Sound and Videoን ልጠቀም?

ከዚህ ቀጥሎ፣ ሶፍትዌሩን ለመጠቀም የሚያገለግሉ ሾርትከት ኪዎችን እንዘረዝራለን።

  • Control O: ፋይል ለመክፈት።
  • Control S: Save Changes.
  • Control Shift S: Save as.
  • Alt Shift 1: የፋይሉን ሳይዝ ለመቀነስ
  • Control W: ፋይሉን ለመዝጋት።
  • Control Shift Q: ማርክ ማድረግን ማስጀመር።
  • Control Shift E: ማርክ ማድረጉን ለማቆም።
  • Control T: ፋይሉን ለመቁረጥ።
  • Control Shift Y: Select All.
  • Control Shift C: Coppy.
  • Control Shift X: Cut.
  • Control Shift V: Paste
  • Control Z: Undo.
  • Control Y: Redo.
  • Control Shift I: ከቪዲዮው ላይ ፎቶ እንደ background ለማስገባት።
  • Control Shift T: ከቪዲዮው ውስጥ ጽሁፍ ለማስገባት።
  • Control Shift P: ከቪዲዮው ውስጥ ኦዲዮ ለማስገባት።
  • Control Shift F: ከቪዲዮው ውስጥ Subtitle ለማስገባት።

ሁሉም ሾርትከቶች እነዚህ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም፣ ሶፍትዌሩን አውርዳቹህ ከጫናቹህ በኋላ ሶፍትዌሩን ከፍታቹህ F1ን ወይም Control F1ን በመንካት፣ ስለሶፍትዌሩ አጠቃቀም በጥልቀት ማወቅ ትችላላቹህ።

ስለሶፍትዌሩ አስተያየት እንፈልጋለን!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

3
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *



error: This Content is protected !!