
ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ለቤተሰቦቻችን ከዚህ ቀደም ከነበሩት አፕሊኬሽኖች የተለየ እና በበርካታ የAI ሞዴሎች የበለጸገውን AI Seek የተባለ መተግበሪያ ልናስተዋውቃችሁ ወደናል።

ይህ አፕሊኬሽን እንደ GPT-5.5፣ Claude 4.7፣ Gemini 3 Pro፣ DeepSeek V4 እና Grok 4.1 ካሉ አለም አቀፍ ታዋቂ ሞዴሎች ጋር በመቀናጀት ከቀላል ቻትቦትነት የላቀ ሁለገብ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload AI Seek from Google Play Store:
ኤአይ ሲክን ለማውረድ ይህንን ይጫኑየAI Seek usage and features
መተግበሪያው ተጠቃሚዎች ከቴክኖሎጂ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች ይሰጣል፦
Image Creation and Editing:

በ Nano Banana 2 እና በ Gemini 3 Pro የተሰራ ሲሆን፣ ጽሁፍን ወደ ምስል ፣ ምስልን ወደ ምስል የስታይል ለውጥ እና የፎቶ ኤዲቲንግ ስራዎችን ማከናወን ያስችላል።
Long-Form Writing Assistant:

የልቦለድ ታሪኮችን ለማቀድ፣ ገጸ-ባህሪያትን ለመፍጠር እና ማራኪ ጽሁፎችን ለማዘጋጀት በ GPT-5.5፣ Claude 4.7 እና DeepSeek አማካኝነት እገዛ ይሰጣል።
AI Fortune-Telling:

ስለ ፍቅር፣ ስራ ወይም ዕለታዊ የዕድል ጥያቄዎችን ለመጠየቅ የሚያስችሉ የ Tarot ንባቦችን፣ የዞዲያክ ትንበያዎችን አካቷል።
Smart Math Solver:
የሂሳብ ጥያቄዎችን በካሜራ በማየት ፈጣን እና ትክክለኛ መልሶችን አፕሊኬሽኑን ተጠቅሞማግኘት ይቻላል።
በአዲሱ የ Version 2.9.4 ላይ የተደረጉ አዳዲስ ለውጦች
አፕሊኬሽኑ በቅርቡ ወደ አዲስ ቨርዥን ያደገ ሲሆን፣ የሚከተሉትን አዳዲስ አቅሞች ጨምሯል፦
ከGoogle Gemini 3 Pro ጋር የተደረገ ውህደት፦
በአዲሱ ማሻሻያ አፕሊኬሽኑ ከGoogle Gemini 3 Pro ጋር በመዋሃዱ እጅግ ፈጣን የሆነ Multi-step reasoning, ለአጠቃቀም ቀላል እንዲሆን እና ረጅም ጽሁፎችን በቀላሉ የማስተናገድ አቅም ተጨምሮለታል። እንዲሁም ይበልጥ ትክክለኛ የሆኑ የፍለጋ ውጤቶችን አፕሊኬሽኑ በቅርቡ በተደረገለት ማሻሻያ አማካኝነት ይሰጣል።
Performance Improvements:
አጠቃላይ የመተግበሪያውን ፍጥነት እና የተጠቃሚ ተሞክሮ የሚያሻሽሉ በርካታ አስፈላጊ ስራዎች ተሰርቷል።
ለዚህ ቴክኖሎጂ አዲስ ለሆናችሁ ተጠቃሚዎች AI Seek ለትምህርት፣ ለፈጠራ ስራዎች፣ ለመዝናኛ እና ለዕለት ተዕለት ችግር ፈቺነት የሚረዳ ድንቅ መፍትሄ ነው።
Leave a Reply