ListenBook: የማይሰሙ የድምጽ ቅጂዎችን ማደሻ ሶፍትዌር!
ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ማንኛውንም ጥራት የሌለውን የድምጽ ፋይል ጥራት ወዳለው ወይም መሰማት ወደሚችል ፋይል መቀየር የሚችልን ሶፍትዌር ለማስተዋወቅ ፈልገናል።
ListenBook ከተቀረጹ ረዥም ጊዜ ያስቆጠሩ፣ የተበላሹ ወይም ጥራታቸው የወረደ የድምጽ ቅጂዎችን የሚያስተካክል እና የሚያድስ ነፃ የ Windows መተግበሪያ ነው። አፕሊኬሽኑ ለaccessibility ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ በ keyboard control መስራት ያስችላል፣ እንዲሁም በEnglish, German, እና Serbian ቋንቋዎች ይሰራል።
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload ListenBook
ListenBookን ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑGeneral information about ListenBook
ብዙ የ audiobook እና የድምጽ ቅጂዎች፣ በተለይም ከ cassette tapes የተቀዱ፣ በቤት ውስጥ የተዘጋጁ፣ ወይም ዝቅተኛ ጥራት ባላቸው መሳሪያዎች የተቀረጹ ኦዲዮዎች ድምፃቸው በጣም ዝቅተኛ፣ ጫጫታ የበዛባቸው ወይም ለማዳመጥ የሚያስቸግሩ ይሆናሉ።
ListenBook የተሰራው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ነው። የማይሰሙ ድምፆችን በመውሰድ የተለያዩ አልጎሪዝሞችን በመጠቀም ወደ ንጹህ፣ ሚዛናዊ እና ወደ ሚሰሙ ኦዲዮ ይቀይራቸዋል።
Features of ListenBook
- ጫጫታዎችን፣ ወይም ዝቅተኛ ጥራት ባላቸው ማይክሮፎኖች ምክንያት የሚፈጠሩ hiss, hum, እና background noise ያስወግዳል። ለዚህም Wiener, Spectral, Median, እና Hybrid የተባሉ አራት አይነት noise-removal algorithms ይጠቀማል።
- ድምፃቸው በጣም ዝቅተኛ ወይም በጣም ከፍተኛ የሆኑ ቅጂዎችን በ automatic volume analysis እና gain correction ያስተካክላል፣ እንዲሁም peak እና RMS normalization ይጠቀማል።
- ለማዳመጥ አስቸጋሪ የሆኑ ወይም የታፈኑ ድምፆችን ለማስተካከል ከ18 በላይ የሆኑ clarity እና EQ presets አሉት። ይህ muddy voices, phone-call-like recordings, እና ሌሎች የድምጽ ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ ይረዳል።
- በስህተት እንደ stereo የተቀመጡ የድሮ mono recordings ካሉ በራሱ detect በማድረግ fake stereo ያስተካክላል።
- over-compressed ለሆኑ ኦዲዮዎች የተዘጋጀ ልዩ recovery path አለው።
How it works?
ፋይሎቻችሁን ወይም ሙሉ ፎልደሩን ወደ መተግበሪያው ማስገባት ብቻ በቂ ነው። ListenBook እያንዳንዱን ቅጂ analyze በማድረግ ትክክለኛውን የ repair settings በራሱ ይጠቁማል፣ ወይም ደግሞ እናንተ ራሳችሁ presets መምረጥ ትችላላችሁ። ስራችሁን ከማጠናቀቃችሁ በፊት የ60 ሰከንድ preview ማዳመጥ ትችላላችሁ፣ በመቀጠልም ሁሉንም በአንድ ላይ በ batch process በማድረግ ወደ MP3, WAV, ወይም FLAC መቀየር ያስችላል።
Shortcut Keys
በዚህ ጽሁፍ ውስጥ፣ አብዛኛዎችን የአፕሊኬሽኑን ሾርትከት ቁልፎችን እንነግራቹሀለን።
- Control O: ፋይል ወደሶፍትዌሩ ለማስገባት።
- Control Shift O: ፎልደር ለማስገባት።
- Control S: ኤዲት የተደረገው ፋይል ሴቭ የሚደረግበትን ፎልደር ለመምረጥ።
- Control T: የ60 ሴኮንድ ፕሪቪዩው ለማዳመጥ።
- Control Shift A: Analyze all (ፕሮግራሙ ምን አይነት ሴቲንግ የድምጽ ፋይሉን ማስተካከል እንደሚችል አናሊሲስ ሰርቶ ይጠቁማል።)
- Control Shift P: ኤዲት ተደርጎ ከተጨረሰ በኋላ፣ ሴቭ የማድረጉን ፕሮሰስ ለማስጀመር።
- Escape: ፕሮሰሱን ለማስቆም።
- Control Shift R: ሁሉንም ሴቲንጎች ወደ ዲፎልት ሴቲንግ ለመመለስ።
- Control Shift S: ኤዲት ለማድረግ የተጠቀምንባቸውን ሴቲንጎች ለወደፊት እንድንጠቀምባቸው ስንፈልግ ወይም ሴቲንጎችን ሴቭ ለማድረግ ስንፈልግ ኮንትሮል ሺፍት ኤስን እንጫናለን።
እዚህ ጽሁፍ ውስጥ፣ ሁሉንም የአፕሊኬሽኑን ሾርትከት ቁልፎችን አላካተትንም። ሶፍትዌሩን ስትጠቀሙት ግር የሚላቹህ ነገር ካለም፣ f1ን በመጫን፣ ስለሶፍትዌሩ አጠቃቀም የሚያስረዳውን ፋይል ይከፍትላቹሀል። ከዚያም ፋይል ሙሉ መረጃ ስለሶፍትዌሩ ማግኘት ትችላላቹህ።
የድሮ audiobook, የቤተሰብ ቅጂ, ወይም ለማዳመጥ የሚያስቸግር የድምጽ ፋይል ካላችሁ ListenBook በጥራት ያድስላችኋል!
አስተያየታቹህን ከአስተያየት መስጫው እንድታሰፍሩልን እንጠይቃለን።
Leave a Reply