
በ 2026 የቴክኖሎጂ አለም ለአካል ጉዳተኞች በተለይም ለዓይነ ስውራን እና የእይታ ውስንነት ላለባቸው ወገኖች ትልቅ የምስራች ይዞ መጥቷል።
Visperoኩባንያ በታዋቂው የ
Jawsላይ እጅግ የረቀቀ የ AI ኤጀንት መጨመሩን ይፋ አድርጓል።
አዲሱ JAWS AI Agent ተጠቃሚዎች ከኮምፒውተራቸው ጋር በተፈጥሯዊ የሰው ልጅ ቋንቋ በቀጥታ እንዲነጋገሩ ያስችላቸዋል።
ይህ ማለት አንድ ተጠቃሚ በስክሪኑ ላይ ያለውን መረጃ ለማግኘት የተለዩ የኪቦርድ ትዕዛዞችን ከመጠቀም ይልቅ፣ ኮምፒውተሩን በቀጥታ ጥያቄ በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት ይችላል።
የዚህ ቴክኖሎጂ ሌላው አስገራሚ ብቃት በስክሪን ላይ የሚታዩ ውስብስብ ምስሎችን እና ግራፎችን በዝርዝር የመግለጽ ችሎታው ነው።
ኤጀንቱ ምስሉ ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን፣ በውስጡ ያሉትን ዝርዝር መረጃዎች እና ቁጥሮች በመተንተን ለተጠቃሚው በድምጽ ያብራራል።
ረጅም ሰነዶችን እና የድረ ገጽ መረጃዎችን በአጭሩ የማጠቃለል ስራንም በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።
ይህም ተጠቃሚዎች ሙሉውን ጽሁፍ ከማንበብ ይልቅ ዋና ዋና ነጥቦቹን በሰከንዶች ውስጥ እንዲረዱ ይረዳቸዋል።
በተጨማሪም የ AI ኤጀንቱ ከዚህ ቀደም ለስክሪን ሪደሮች አስቸጋሪ የነበሩ ውስብስብ ድረ ገጾችን እና አፕሊኬሽኖችን በቀላሉ የመረዳት ብቃት አለው።
ይህ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች በስራ ቦታም ሆነ በትምህርት ቤት ያላቸውን ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።
በአጠቃላይ የ JAWS AI Agent መምጣት የዲጂታል አለምን ለሁሉም ሰው እኩል ተደራሽ ለማድረግ የተደረገ ትልቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው።
ይህ አዲስ አሰራር የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሰዎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ለማቃለል ያለውን እምቅ አቅም በተግባር ያሳየበት ክስተት ነው።
በዚህ ማሻሻያ ምክኒያት የJaws ተፎካካሪ የሆነው NVDA ከምርጫ ውጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እስኪ በዚህ ዙሪያ ላይ Comment section ላይ ተወያዩበት።
አሁን ደግሞ የኤአይ ኤጀንቱን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በአጭሩ የሚያስረዳውን ድምጽ ያድምጡ።
Leave a Reply