G Tech Ethiopia – Blog

Bookworm new update: 2026.1

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ በተለይ ለአይነስውራን ኮምፒውተር ተጠቃሚዎች በአዲሱ የBookworm Update ላይ የተጨመሩ አዳዲስ ነገሮችን ይዘንላችሁ መጥተናል።

Bookworm 2026.1 አሁን በይፋ Release ሆኗል።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

Download Bookworm 2026.1

ቡክዎርምን ከዚህ ዌብሳይት ማግኘት ትችላላቹህ። ማለትም፣ የፖርቴብል ቨርዥኑን እና የstandard setup ቨርዥኑን በቀጥታ ማውረድ ትችላላቹህ። አሁን ላይ፣ የቡክዎርም ዲቨሎፐሮች ለሁለቱም የኮምፒውተር CPU Architectures (32 bit እና 64 Bit) ስላዘጋጁ፣ እኛም ለእናንተ ለማውረድ እንዲቀላቹህ እንደሚከተለው ሊንኮችን እናጋራቹሀለን።

  1. 64 Bit ኮምፒውተር ያላቹህ ይህንን ሊንክ ተጠቀሙ
  2. የ64 bit ፖርቴብል ቨርዥኑን ለማውረድ ይሄንን ሊንክ ተጠቀሙ
  3. 32 bit ኮምፒውተር ያላቹህ ይሄንን ሊንክ ተጠቀሙ
  4. የ32 bit ፖርቴብል ቨርዥኑን ለማውረድ፣ ይሄንን ሊንክ ይጠቀሙ።

Bookworm እንደ PDF, EPUB, MOBI እና DOCX ያሉ ከ20 በላይ የሚሆኑ የፋይል አይነቶችን ያለምንም ችግር ለማንበብ የሚያስችል ምርጥ Document Reader ነው። በተለይ ለ Accessibility ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ የተሰራ በመሆኑ ብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ ተመራጭ ነው።

በዚህ አዲስ Version ላይ የተካተቱ ዋና ዋና ማሻሻያዎችን እንደሚከተለው አቅርበናቸዋል።

New features

  • የ OCR ብቃት መሻሻል: በአዲሱ ስሪት የ OCR ብቃቱ እጅግ እንዲጨምር ተደርጓል። አሁን ላይ እንደ Baidu OCR እና Vivo OCR ያሉ አዳዲስ Engines ተካተዋል። ይህም ጽሁፍ ያላቸውን ምስሎች ወደ ተነባቢ ጽሁፍ የመቀየር ስራውን ይበልጥ ፈጣን እና አስተማማኝ ያደርገዋል።
  • Media Key Control: ሌላው ደስ የሚለው ነገር፣ የTTS ቁጥጥር ላይ የተደረገው ለውጥ ነው። አሁን በኮምፒውተራችሁ ላይ ያሉትን Media Keys በመጠቀም ንባቡን በቀላሉ Play እና Pause ማድረግ ትችላላችሁ። ይህ Global እና Local Media Key Support ማድረጉ በስራ ወቅት ትልቅ ምቾት ይሰጣል።
  • Bookmarks እና Comments: አሁን Bookmarks ማንበብ በቆሙበት ቦታ መሰረት Sort ስለሚደረጉ የፈለጉትን ቦታ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም፣ Comments አሰጣጡ ይበልጥ Detailed ሆኗል፤ በአንድ መስመር ውስጥ ባለ የተወሰነ የጽሁፍ ክፍል ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ አስተያየት መስጠት ተችሏል።
  • Bug Fixes: ከዚህ ቀደም በ EPUB እና በ Word ፋይሎች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ጥቃቅን Bugs ተስተካክለዋል። በተለይ የ Documents cache አያያዝ እና የ Metadata አቀራረብ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጓል።

ይህ Update የነበሩ ክፍተቶችን በመድፈን የBookworm ተጠቃሚዎች የተሻለ የንባብ ልምድ እንዲኖራቸው ያደርጋል።

ስለ Bookworm አዲስ Update ያላችሁን አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

1
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *