ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ በተለይ ለ NVDA Screen Reader ተጠቃሚዎች የቲክቶክ ቪዲዮዎችን በቀላሉ እና በተደራሽ ሁኔታ ለማውረድ የሚረዳ አንድ እጅግ ጠቃሚ Add-on ይዘንላችሁ መጥተናል።
ብዙዎቻችን ቲክቶክ ላይ የምናገኛቸውን ቪዲዮዎች ሴቭ ለማድረግ እንቸገራለን። በተለይ ደግሞ ለ Screen Reader ተጠቃሚዎች ነገሩ ይበልጥ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። TikTok Downloader for NVDA ይህንን ችግር ለመቅረፍ የተሰራ ምርጥ Tool ነው።
Follow us on Telegram
Join Our Telegram ChannelDownload Tiktok downloader
የቲክቶክ ቪዲዮዎችን ማውረድ የሚችለውን የኤንቪዲኤ አዶንን ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ።የ TikTok Downloader ዋና ዋና Features
ይህ Add-on ቪዲዮዎችን ከማውረድ ባለፈ ለተጠቃሚዎች ምቾት የሚሰጡ በርካታ ማሻሻያዎችን አካቷል።
- Video Download: ቪዲዮዎችን በ MP4 Format ጥራታቸውን ሳይቀንሱ ማውረድ ያስችላል።
- Watermark-Free Option: የቲክቶክ ምልክት ወይም Watermark የሌለባቸውን ቪዲዮዎች ለማውረድ ይሞክራል።
- Quality Selection: እንደ ፍላጎታችሁ የቪዲዮውን ጥራት (Best, 1080p, 720p, 480p, ወይም 360p) መምረጥ ትችላላችሁ።
- Smart URL Detection: ከ Browser address bar ወይም ከ Clipboard ላይ የቲክቶክ URL በራሱ Detect የማድረግ ብቃት አለው።
- Background Downloads: ቪዲዮው እስኪወርድ ድረስ መጠበቅ አያስፈልጋችሁም። በ Background እየወረደ እናንተ ሌሎች ስራዎችን መስራት ትችላላችሁ።
- Sound Notifications: Download ሲጀምር፣ ሲያልቅ ወይም Error ሲያጋጥም በድምፅ ያሳውቃቹሃል።
- Download Queue: በአንድ ጊዜ ብዙ ቪዲዮዎች እንዲወርዱ ማድረግ ይቻላል።
አጠቃቀም እና Keyboard Shortcuts
ይህንን Add-on ለመጠቀም በጣም ቀላል የሆኑ Shortcuts ተዘጋጅተውለታል።
- NVDA+Shift+T: የ TikTok Downloader Dialog ለመክፈት
- እዚህ ላይ አንዴ ታብን ስንጫን የቲክቶክ ቪዲዮውን ሊንክ የምናስገባበት ቦታ እናገኛለን።
- ቀጥሎ፣ አሁንም ታብን ስንነካ፣ የቪዲዮውን ጥራት የምንመርጥበት ቦታ ይመጣልናል።
- ቪዲዮውን ስናወርድ የቲክቶክ መለያ ምልክትን ለማጥፋት ስንፈልግ፣
Try to remove watermark
የሚለውን checkbox ስፔስን በመንካት ቼክ እናደርግና ታብን በመንካትAdd to Download Q
የሚለውን በተን በመንካት ቪዲዮውን ማውረድ መጀመር ይቻላል። - NVDA+Shift+Control+T: ከ Clipboard ላይ ያለን ሊንክ ወዲያውኑ ማውረድ ለመጀመር (Quick Download)
- Delete: የተመረጠውን Download ዝርዝር ውስጥ ለማጥፋት
አጫጫን እና Requirements
አዶኑ በስራ ላይ እንዲውል የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
- NVDA 2019.3 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ Version።
- Windows 10 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ኦፕሬቲንግ ሲስተም።
አጫጫን
- የቅርብ ጊዜውን .nvda-addon ፋይል
ከዚህ ዌብሳይት ላይ ዳውንሎድ ያድርጉ። - NVDA እየሰራ ባለበት ሁኔታ ፋይሉን ይክፈቱት።
- የሚመጣላችሁን የአዶን ኢንስቶሌሽን ጥያቄ Confirm በማድረግ NVDA Restart እንዲሆን ያድርጉ።
ይህንን ጠቃሚ Add-on አሁኑኑ ጭናችሁ በመጠቀም የቲክቶክ ቪዲዮዎችን ያለ ምንም እንግልት ማውረድ ትችላላችሁ። ስላላችሁ አጠቃቀም ወይም ስላጋጠማችሁ ችግር በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!
Leave a Reply