
Windows Terminal በአሁኑ ሰዓት ለ Windows ተጠቃሚዎች በተለይም ለ Power users እና ለ Developers እጅግ ወሳኝ software ነው። ይህ መተግበሪያ እንደ Command Prompt: PowerShell እና WSL ያሉ የተለያዩ Tools በአንድ ቦታ በማቀናጀት ስራን ያቀላጥፋል። ዛሬ ደግሞ አጠቃቀማችሁን ይበልጥ ፕሮፌሽናል የሚያደርጉ አምስት ምርጥ Commands ይዘንላችሁ መጥተናል።
Follow us on telegram
Join our Telegram Channelአንደኛው እና ዋነኛው wt Command ነው። ይህ ትዕዛዝ Windows Terminal የትም ቦታ ሆናችሁ በፍጥነት ለመክፈት ይረዳችኋል። ለምሳሌ Run dialog box ላይ ወይም Command Prompt ላይ በመሆን “wt” ብላችሁ ስትጽፉ ተርሚናሉ ይከፈታል። በተጨማሪም በምትከፍቱበት ወቅት በተለየ Profile እንዲከፈት ከፈለጋችሁ wt -p “PowerShell” የሚለውን በመጠቀም ስራችሁን መጀመር ትችላላችሁ።
ቀጣዩ እና እጅግ ጠቃሚው Command explorer . ነው። በ Terminal ውስጥ ስራችሁን እየሰራችሁ ሳለ ድንገት ወደ Graphical User Interface (GUI) መመለስ ቢፈልጉ ይህ Command በዚያ ሰዓት ያላችሁበትን Folder በ Windows File Explorer ውስጥ ወዲያውኑ ይከፍትላችኋል። ይህም ከ Directory ወደ Directory በመፈለግ የሚባክነውን ጊዜ በእጅጉ ይቆጥባል።
ለ Developers ደግሞ code . እጅግ አስፈላጊ Command ነው። ይህ ትዕዛዝ በምትሰሩበት Folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን በቀጥታ በ Visual Studio Code ለመክፈት ያገለግላል። ተርሚናሉ ላይ ሆነው “code .” ብለው ሲጽፉ ኤዲተሩ ከነሙሉ ፕሮጀክቱ ወዲያውኑ ይከፈታል።
ሌላው ማወቅ ያለባችሁ winget የተባለው Package manager ነው። አዳዲስ Softwares ለመጫን፣ ለማጥፋት ወይም Update ለማድረግ ወደ ተለያዩ Websites መሄድ ሳያስፈልጋችሁ በቀጥታ በ Terminal ውስጥ ስራችሁን መጨረስ ትችላላችሁ። ለምሳሌ ሁሉንም አፖች በአንድ ጊዜ Update ለማድረግ winget upgrade –all የሚለውን መጠቀም በቂ ነው።
ተርሚናሉ በጽሁፎች ሲጨናነቅ እና ነገሮችን ግልጽ ማድረግ ሲፈልጉ cls ወይም clear የሚለውን Command መጠቀም ትችላላችሁ። ይህ አነስተኛ ቢመስልም በስራ ላይ ትኩረት ለማድረግ እና ንጹህ ስክሪን እንዲኖራችሁ ይረዳል።
በተጨማሪም እንደ Ctrl + Shift + F ያሉ Shortcuts በመጠቀም በ Terminal ውስጥ ያሉ ጽሁፎችን በፍጥነት መፈለግ ይቻላል። እነዚህን Commands በመለማመድ የ Windows Terminal አጠቃቀማችሁን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ትችላላችሁ።
Leave a Reply