G Tech Ethiopia – Blog

Ferda Screen Reader: New alternative for Android Phones

Screenshot of Ferda screen reader

Ferda Screen Reader: ለዓይነስውራን ወገኖች የተዘጋጀ አዲስ እና ዘመናዊ መተግበሪያ!

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ የአንድሮይድ ስልካችሁን Accessibility ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር አዲስ መተግበሪያ ይዘንላችሁ መጥተናል።

ይህ መተግበሪያ Ferda Screen Reader የሚባል ሲሆን፣ በMustafa Doğan ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተሰራ ነው።

Ferda Screen Reader እጅግ ፈጣን፣ ቀላል እና የተጠቃሚዎችን የግል ሚስጥር ለመጠበቅ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ መተግበሪያ ነው። አላስፈላጊ የሆኑ Permissions የሌሉበት በመሆኑ ለደህንነትዎ ሳይሰጉ በ Play Store ላይ አግኝተው ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

ፈርዳ ስክሪን ሪደርን ያውርዱ

ፈርዳ ስክሪን ሪደርን በፕለይ ስቶር ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ

Features of Ferda Screen Reader :

  • ፍጹም የሆነ Privacy: ከስልኮች መረጃ መሰብሰብ የእኛ ቀይ መስመር ነው በሚለው መርህ የሚሰራው ይህ አፕ፣ ምንም አይነት መረጃዎችን ወደ ሶስተኛ ወገን አይልክም። ሁሉም ሂደቶች የሚከናወኑት በራሱ በስልኩ ላይ ብቻ ነው።
  • Smart Microphone Management: የድምጽ መልዕክት እየላኩ ወይም በድምጽ ትእዛዝ እየሰጡ ባሉበት ወቅት፣ የ Screen Reader ድምጽ እንዳይገባ ወይም ስክሪኑን እስካልነኩት ድረስ ዝም እንዲል ተደርጎ ተሰርቷል።
  • Advanced Clipboard Management: በሌሎች Screen Readers ላይ የማይገኝ አዲስ Feature ሲሆን፣ ብዙ ጽሁፎችን Clipboard ላይ Append በማድረግ፣ በፈለጉት ቦታ ላይ ሁሉንም በአንድ ጊዜ Paste ማድረግ ያስችልዎታል።
  • Offline Translation and Dictation: ኢንተርኔት ወይም SIM ካርድ በሌለበት ሁኔታ እንኳ፣ በስክሪኑ ላይ ያሉ የውጭ ቋንቋዎችን መተርጎም እና የድምጽ ጽሁፍን መጠቀም ይችላሉ።
  • Image-to-Text (OCR): በስክሪንዎ ላይ ጽሁፍ ያለበት ምስል ካለ፣ በአንድ የጣት እንቅስቃሴ ብቻ በምስሉ ላይ ያለውን ጽሁፍ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
  • Quick Access and Subtitle Support: በአንድ Gesture ብቻ ስልኩን መቆለፍ፣ ሰዓት፣ ቀን እና የባትሪ ሁኔታን ማየት ይቻላል። በተጨማሪም እንደ YouTube ባሉ Platforms ላይ የ Subtitle Reading support አለው።

ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነጥብ

Ferda Screen Reader በምስሎች ውስጥ ያሉ የ IBAN ቁጥሮችን፣ ሙሉ ስሞችን፣ የ Email አድራሻዎችን እና የስልክ ቁጥሮችን ለይቶ የማወቅ እና ኮፒ የማድረግ ልዩ Feature አለው። ይህ Feature በሌሎች የሞባይል Screen Readers ላይ የማይገኝ በመሆኑ ለተጠቃሚዎች እጅግ ጠቃሚ ነው።

ይህ Screen reader በክፍያ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች አሉት።

Pro VS free version of the app

  1. Copy /pasting, |Clipboard history
  2. አንድን ነገር ኮፒ ካደረጋቹህ በኋላ ከጊዜ በኋላ Access ለማድረግ ከፈለጋቹህ፣ የpremium Feature መግዛት ይጠበቅባቹሃል።

  3. Offline Translation and OCR
  4. ዖፍላይን ትርጉም እና የኦሲአር አገልግሎት ለማግኘት የPremium Version ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል። አንድን ጽሁፍ ለመተርጎም፣ መተግበሪያው ፋይል ያወርዳል። ይህንን ግን ለማግኘት በወር 2:00 Dollars ወይም 19:00 በአመት መክፈል ይጠበቅባቹሃል።

በአጠቃላይ፣ የዚህ መተግበሪያ ጀስቸሩ ከቶክባክ ጋር ከሞላ ጎደል አይለይም። ነገር ግን፣ ይህ መተግበሪያ ከቶክባክ ጋር ሲነጻጸር እጅግ Responsive ነው።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

1
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *