G Tech Ethiopia – Blog

ዋትስአፕ የአካውንቶችን ደህንነት ይበልጥ ለማጠናከር “የአካውንት ይለፍ ቃል” (Account Password) የተሰኘ አዲስ አገልግሎት እያዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

ዋትስአፕ ተጠቃሚዎች ለአካውንታቸው ተጨማሪ የጥበቃ ንብርብር እንዲኖራቸው የሚያስችል አዲስ አሰራር እየቀረጸ ነው። ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደፈለጉ ሊጠቀሙበት የሚችሉት (Optional) ሲሆን፣ አሁን ካለው ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (two step verification) ጋር ተዳምሮ የተሻለ ደህንነትን ለመፍጠር የታለመ ነው።

ሥለአገልግሎቱ መግለጫ

ተጠቃሚዎች የሚመርጡት የይለፍ ቃል ከፊደላትና ከቁጥሮች የተመሰረተ መሆን አለበት። ርዝመቱም ከ6 እስከ 20 ቁምፊዎች (characters) መሆን ሲኖርበት፣ ቢያንስ አንድ ፊደልና አንድ ቁጥር ማካተት ይኖርበታል።

የአገልግሎቱ አጠቃቀም

አንድ ተጠቃሚ ወደ አካውንቱ ለመግባት ሲሞክር፣ መደበኛውን የ6 አሃዝ ኮድ ካስገባ በኋላ ይህንን የይለፍ ቃል እንዲያስገባ ይጠየቃል። ተጠቃሚው ቀድሞውኑ ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫን አብርቶ ከሆነ፣ መጀመሪያ እሱን ካስገባ በኋላ የይለፍ ቃሉን እንዲሞላ ይደረጋል።

አገልግሎቱ አሁን ላይ ይገኛል?

ይህ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት በልማት (under development) ላይ ያለ በመሆኑ፣ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ገና አልተለቀቀም። በቅርቡ በሚወጡ የዋትስአፕ የሙከራ ስሪቶች (Beta versions) እና ቀጥሎም ለሁሉም ተጠቃሚዎች ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ አዲስ አሰራር በተለይ ስልካቸው በሌላ ሰው እጅ ቢገባ ወይም ሲም ካርዳቸው ቢጠለፍ እንኳ፣ ያለ ይለፍ ቃሉ አካውንታቸውን ማንም እንዳይከፍተው ለመከላከል ይረዳል።

አስተያየታቹህን አስቀምጡልኝ!

Provided by:


ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *