ጠቃሚ የሆኑ productivity tools, document utilities, OCR, audio features እና accessibility functions በአንድ ላይ የያዘ አንድ Android app ማግኘት ሁልጊዜም ቀላል አይደለም።
ብዙ አፖች በአንድ የተወሰነ ስራ ላይ ብቻ ትኩረት ስለሚያደርጉ ተጠቃሚዎች የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ለማከናወን የተለያዩ አፖችን install ማድረግ ይገደዳሉ።
OmniCore ግን የተለየ መንገድ ይከተላል።
በ Shukla Tech Group develop የተደረገው ይህ Android app እጅግ ብዙ text, audio, document, navigation, calculation እና accessibility tools በአንድ ላይ አጣምሮ ይዟል።
አፑ Google Play ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ 1,000 በላይ downloads ተደርጓል።
Listen to this article
Loading voices…
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload OmniCore from Google Play:
OmniCoreን ለማውረድ፣ ይህንን ሊንክ ይጫኑOmniCore ምንድን ነው?
OmniCore እራሱን እንደ Smart Text, Audio & Document Tools ስብስብ ነው የሚገልጸው። በአንድ የተወሰነ function ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ እንደ multi-purpose utility app ያገለግላል። የአሁኑ version አራት ዋና ዋና የ functionality ምድቦችን ያካትታል:
- Smart Accessibility
- Documents and PDFs
- Daily Utilities
- Smart Vision
በተጨማሪም፣ የመተግበሪያው developer መተግበሪያው በspeed, privacy እና local processing ላይ ትልቅ ትኩረት በማድረግ፣ መተግበሪያው ለአጠቃቀም ምቹ እንዲሆን ጥረት አድርጓል።።
በ Google Play መረጃ መሰረት የአፑ ተግባራት ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚው device ላይ እንዲከናወን ተደርጎ ነው design የተደረገው።
ለ Blind እና Low-Vision ተጠቃሚዎች የተዘጋጁ Accessibility Features
ከመተግበሪያው አስደናቂ ጥቅሞች መካከል አንዱ የተለያዩ የAccessibility features ማካተቱ ነው። የመተግበሪያው አበልጻጊ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ OmniCore ማየት ለተሳናቸው እና low-vision ለሆኑ ተጠቃሚዎች የሚረዱ features ለማቅረብ የ Android AccessibilityService API ይጠቀማል።
ከነዚህ features አንዱ Smart Copy ሲሆን መደበኛ text selection አስቸጋሪ በሆነባቸው አፖች ላይ text select እና copy ለማድረግ ይረዳል። ሌላኛው feature ደግሞ Virtual Screen ነው። እንደ አበልጻጊው ማብራሪያ፣ ይህ feature በ screen ላይ ያሉ አገልግሎቶቻቸውን ለማወቅ የማንችላቸውን text እና buttons identify በማድረግ የበተኖቹን ስም Accessible እንዲሆኑ ያደርጋል።
እንዲሁም፣ ተጠቃሚዎች የተወሰነውን የስክሪኑን ክፍል scan እንዲያደርጉ የሚያስችለው Smart Focus OCR ተካቷል። ዲቨሎፐሩ እንደሚለው፣ ይህን feature የ Volume Up button ተጭኖ በመያዝ activate ማድረግ ይቻላል።
OmniCore ስልኩን ለማጥፋት power control ከመጫን ይልቅ ስልኩን በማወዛወዝ lock ማድረግ የሚያስችል Smart Lock አለው። በተጨማሪም፣ ስለ battery status በድምጽ የሚነግር Battery Announcer ያካተተ ሲሆን፣ Time Announcer እና Voice Reminder የተባሉ አገልግሎቶችን በነጻ ያቀርባል። በእነዚህ ምክኒያቶች፣ OmniCore ከ accessibility አኳያ እጅግ ጠቃሚ መተግበሪያ እንዲሆን አስተዋጽዖ አበርክተዋል።
Text and Audio Tools
OmniCore ከ text ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ tools ያሉት ሲሆን፣ ከtext ጋር የተያያዙት features የሚከተሉት ናቸው:
- Smart Copy
- Smart Paste
- Smart Edit Text
- Clipboard History
- Smart Notepad
- Smart Link Saver
አፑ ረዣዥም ጽሁፎችን ወደ WAV ወይም ወደ ድምጽ መቀየር የሚያስችል Text to Audio Creator የሚባል አገልግሎት በውስጡ ይዟል።
PDF እና Document Tools
OmniCore በርካታ የሆኑ standalone document አፖችን ለመተካትም ይሞክራል። በdocument functionality ስር document scanner እና document reader አካቷል። ይህ reader ከ PDFs እና text files ጋር መስራት የሚችል ሲሆን፣ ይዘቶቹን በድምጽ ለማዳመጥ የሚያስችል Audio Mode አለው። አፑ የሚከተሉትን በርካታ የ PDF አገልግሎቶችን ይሰጣል:
- Compressing PDFs
- Merging PDFs
- Locking PDFs
- Unlocking PDFs
- Converting images to PDF
- Converting PDFs to images
- Document conversion
በተጨማሪም ለ compression, cropping እና enhancement የሚያገለግሉ የ image-processing tools አሉት።
እነዚህ አገልግሎቶች በስልካቸው ብዙ documents ለሚቀበሉ እና ለእያንዳንዱ የ document ስራ የተለያየ app install ማድረግ ለማይፈልጉ ተማሪዎች, professionals እና ሌሎች ተጠቃሚዎች በጣም ጠቃሚ ነው።
Calculators እና Everyday Utilities
ሌላኛው የ OmniCore ትልቁ ክፍል የ calculators Feature ነው። አሁን ባለው የ Google Play መረጃ መሰረት፣ የአፑ calculator እንደ percentage calculations, discounts, age calculations, loans, profit and loss, income tax, electricity, fuel, BMI, land area, currency እና ሌሎች financial ወይም የዕለት ተዕለት calculations በብቃት ማከናወን ይችላል።
Navigation Features
አፑ ከ navigation ጋር የተያያዙ የሚከተሉትን tools ይዟል:
- Where Am I
- Compass
- Speedometer
- Nearby
- Live Tracking
Smart Vision Features
OmniCore የተለያዩ camera እና visual-information መስጠት የሚችሉ tools በውስጡ ይዟል። የዚህ አፕ Smart Camera ከ voice guidance ጋር Portrait, HDR, Night እና Beauty modes የተባሉ የፎቶ ኢፌክቶችን ተጠቅመን ፎቶ ያለማንም ርዳታ ማንሳት እንችላለን። በተጨማሪም የ Indian currency ማሳወቂያ የሆነ Cash Reader አለው። ስለዚህ ይህ የተለየ feature በሌሎች ሀገራት ከሚገኙ ገንዘቦች ይልቅ Indian rupees ለሚጠቀሙ ሰዎች እጅግ ጠቃሚ ነው። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የ OmniCore accessibility እና productivity features በመላው አለም ላይ ጠቃሚ ቢሆኑም Cash Reader የተባለው የመተግበሪያው አገልግሎት፣ የህንድን መገበያያ ገንዘብን ብቻ እንዲለይ ተደርጎ የተሰራ አገልግሎት ስለሆነ ለእኛ ሀገር ተጠቃሚ አገልግሎቱ አይጠቅምም።
Leave a Reply