ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ በርካታ productivity tools በአንድ Application ውስጥ ያካተተ Smart Typer የተባለ ድንቅ Android app ይዘንላችሁ ቀርበናል።
Listen to this article
Loading voices…
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload Smart Typer from Google PlayStore:
ስማርት ታይፐርን ከፕለይ ስቶር ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑSmart Typer ምንድን ነው?
Smart Typer የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም notes management, accessible እና precise text editing, text-document conversion, እንዲሁም AI-powered functionalities በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ የ Android app ነው።
ዋና ዋና አገልግሎቶች
File & Directory Management
አዳዲስ files እና folders አፕሊኬሽኑ ለመፍጠር ያስችላል። በተጨማሪም፣ በማንኛውም file ወይም folder ላይ long-press በማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚያስችል contextual menu ይከፍታል፤ በዚህም መሰረት Edit የሚለውን option በመምረጥ ማናቸውንም text-type file ወይም Microsoft Word ከፍቶ በቀላሉ ኤዲት ማድረግ የምንችልበትን መንገድ አፕሊኬሽኑ አመቻችቶልናል።
አስባችሁታል፣ የማይክሮሶፍት ወርድ ፋይሎችን በቀላሉ ስልካችንን ብቻ ተጠቅመን ኤዲት ስናደርግ?
Convert to PDF የሚለውን Feature በመጠቀም ደግሞ አንድን ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ files ወደ PDF format መቀየር ይቻላል። ፋይላችንን ወደ PDF ስንቀይር color themes, font size, margins, page size እና orientation ማስተካከል እንድንችል አፕሊኬሽኑ ማስቻሉ፣ ከሌሎች ፋይልን ወደ PDF ከሚቀይሩ ሌሎች አፕሊኬሽኖች ለየት የሚያደርገውና የሚያስመርጠው ነው።
Convert to Handwriting አማራጭን በመጠቀም ደግሞ ዲጂታል ጽሁፎችን ወደ የእጅ ጽሁፍ መቀየር ያስችላል። ማለትም፣ ለእኛ አንድን ጽሁፍ በእጅ የተጻፈ ማስመሰል ካለሶፍትዌር እገዛ መቀየር አንችልም። አሁን ላይ ይህን ችግር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ይህ አፕሊኬሽን መቅረፍ ይችላል። ለምሳሌ አንድ አይነስውር ተማሪ በመምህሩ አንድ አሳይመንት እንዲሰራ ሲታዘዝና አሳይመንቱ ደግሞ በእጅ ተጽፎ እንዲገባ የሚል ቢሆን፣ ግዴታ የሌላ ሰው ርዳታ ያስፈልገዋል። ካሁን በኋላ ግን ይህንን አፕሊኬሽን በመጠቀም በዲጂታል ዲቫይሶች የተጻፈውን ጽሁፍ ያለማንም ርዳታ ይህንን አፕሊኬሽን በመጠቀም ብቻ መቀየር ይችላል።
Convert to Audio & Media Players የሚለውን በመጠቀም የፈለግነውን ጽሁፍ ወደ ማይክሮሶፍት ድምጾች መቀየር እንችላለን። ማለትም የአማርኛ ጽሁፎችን የማይክሮሶፍት መቅደስ እና አማሃን በመጠቀም፣ ጽሁፎቻችንን ማስነበብ እንችላለን። ይህ አገልግሎት ያለምንም ገደብ መጠቀም እንችላለን።
እንዲሁም፣ አፕሊኬሽኑ የራሱ የሆነ ሚዲያ ፕለየር ያለው ሲሆን፣ ፕለየሩ ደግሞ የተለያዩ የድምጽ ፋይሎችንና ቪዲዮዎችን ማጫወት ይችላል። play button ላይ long-press በማድረግ የድምጹን ፍጥነት ከ 0.5x እስከ 2.0x ማስተካከል ይቻላል። ወደ ፊት እና ወደ ኋላ ማሳለፊያ seek buttons ላይ long-press በማድረግ ደግሞ መዝለያ skip intervals (5s, 10s, 15s, 30s, 60s) ማስተካከል ያስችላል።
Universal Operations የሚባለውን feature በመጠቀም አንድን ፋይል ወይም በአንዴ የተለያዩ ፋይሎችን copy, paste, move, rename, share, እና delete ማድረግ ይቻላል።
In-Built Accessible Text Editor
ይህ text editor ሁለት የተለያዩ modes አሉት። እነሱም ለመደበኛ ማስታወሻዎች እና ኮዶች የሚያገለግል standard text editing፣ እንዲሁም simplified markup ወደ HTML, Markdown, ወይም WordPress blog posts የሚቀይር blogger mode ናቸው። በተጨማሪም፣ በርካታ ጽሁፎችን በአንድ ላይ bulk block formatting ለማድረግ የሚያስችል multi-selection range mode በውስጡ አካቷል።
አፕሊኬሽኑ ከድምጽ ወደ ጽሁፍ መቀየር የሚያስችል ሲሆን፣ ታዲያ እያወራን አፕሊኬሽኑ ጽሁፍ እንዲጽፍልን ከፈለግን፣ የMic ምልክቱን መጫን ብቻ በቂ ሲሆን ይህ አገልግሎት offline ወይም online ይሰራል። የMic ምልክቱን long-press በማድረግ ደግሞ favorite ቋንቋዎችን መቀያየር ይቻላል። Intelligent Offline Text Corrector በመጠቀም voice typing ሲጠናቀቅ በድምጽ የገቡ ስህተቶችን በራሱ ጊዜ ያስተካክላል።
AI Text Processing የሚባለው feature ደግሞ የተጻፉ ጽሁፎችን አራት የተለያዩ AI modes በመጠቀም ስህተቶችን የኤአይ አገልግሎትን በመጠቀም ያስተካክላል። Default የሚባለው Mode አጠቃላይ የሰዋሰው እና የፊደል አጻጻፍ ስህተቶችን ለማስተካከል የሚረዳ ሲሆን፣ Formalise and Translate የሚባለው mode ደግሞ የጽሁፉን style ከማሳመር በተጨማሪ ከተለያዩ ቋንቋዎች ወደ English ይተረጉማል። Intelligent Contextual Writer mode ደግሞ ለ articles ወይም blogs የሚሆኑ ጽሁፎችን ያስተካክላል እንዲሁም መረጃዎችን እውነተኛ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላል።
Features via Navigation Drawer
Instant Translate በማድረግ Google ወይም Microsoft translation services በመጠቀም ጽሁፎችን ወደተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎም ይቻላል። ይህም በቀላሉ ቋንቋዎችን መፈለግ የሚያስችል searchable language selection dropdown አለው።
AI Typing Assistant: አስፈላጊ የሆነ workspace ሲሆን ለ voice typing, AI text enhancement, translation, እና ይህንን አገልግሎት ተጠቅመን የጻፍናቸውን ጽሁፎች በቀጥታ ወደ WhatsApp share ለማድረግ ያገለግላል።
በWikipedia Search አማካኝነት ማንኛውንም ርዕስ Wikipedia ላይ መፈለግ፣ መምረጥ፣ ማንበብ፣ ወይም በቀጥታ ወደ notes ማስገባት ይቻላል። ይህም feature መፈለጊያ ያለው language selection spinner ያካተተ ነው።
Word Helper የሚባለው አገልግሎት ደግሞ በ AI-powered የሆነ dictionary tool ሲሆን የቃላት ፍቺ፣ ተመሳሳይ እና ተቃራኒ ቃላት ያቀርባል።
Extensive Format & System Integration
ይህ app በርካታ የፋይል አይነቶችን ይከፍታል። ከነዚህም ውስጥ
- plain text (.txt),
- Markdown (.md),
- HTML,
- JSON,
- XML,
- YAML,
- CSV,
- Log,
- INI,
- PHP,
- JS,
- Python (.py),
- Shell (.sh),
- CSS, እና
- Microsoft Word (.docx) documents ይገኙበታል።
በመጨረሻም በ application settings በኩል dark እና light themes, automatic note titling, ማስታወሻዎቹ export ሲደረጉ፣ auto-saving ማድረግ፣ emoji intensity ማስተካከል፣ እና የ default ቋንቋዎችን መምረጥ ይቻላል።
Leave a Reply