
Google ለ Windows ተጠቃሚዎች አዲስ የ Search App ይፋ አደረገ!
ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ለ Windows ተጠቃሚዎች እጅግ ደስ የሚል ዜና ይዘንላችሁ መጥተናል። Google ለመጀመሪያ ጊዜ ለ Windows OS ተጠቃሚዎች ተብሎ የተሰራ Native Search App መልቀቁን በይፋ አስታውቋል።
Follow us on Telegram
Join our Telegram ChannelDownload Google app for Windows
ጉግል ለኮምፒውተር የሰራውን አፕሊኬሽን ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ።ይህ አዲስ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች Browser ሳይከፍቱ በቀጥታ ከ Desktop ላይ መረጃዎችን በፍጥነት እንዲፈልጉ ለማስቻል ታስቦ የተሰራ ነው። አሰራሩም ለ Windows system በሚመች መልኩ የተቀረጸ ነው።
አዲሱ የ Google App በውስጡ የ Gemini AI ድጋፍን በከፍተኛ ደረጃ አካቶ ይዟል። ይህም ማለት ተጠቃሚዎች ከወትሮው የ Search ልምድ ባለፈ ውስብስብ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ረጅም ጽሁፎችን ለማጠቃለል ወይም አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት በቀጥታ መተግበሪያውን መጠቀም ይችላሉ።
መተግበሪያው ለተጠቃሚዎች ምቹ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ በ Windows Taskbar ወይም Start Menu ላይ Pin በማድረግ በፍጥነት መክፈት ይቻላል። ይህም በየቀኑ የምናደርገውን የ Search ሂደት እጅግ ቀልጣፋ እና ፈጣን ያደርገዋል።
ከ Search በተጨማሪ፣ አፑ የ Google Discover ባህሪን በውስጡ ይዟል። በዚህም ተጠቃሚዎች እንደ ፍላጎታቸው የተመረጡ ዜናዎችን፣ የአየር ሁኔታ መረጃዎችን እና የፋይናንስ ሁኔታዎችን በቀጥታ ከ Desktop ማግኘት ይችላሉ።
በ Privacy እና Security ረገድም አፑ ጠንካራ መቆጣጠሪያዎችን ይዟል። ተጠቃሚዎች የ Search Historyያቸውን በቀላሉ እንዲያጠፉ ወይም ማንነታቸው ሳይታወቅ እንዲፈልጉ የሚያስችሉ የ Incognito Shortcuts በመተግበሪያው ላይ ተካተዋል።
በተያያዘ ዜና Google ለ Mac ተጠቃሚዎችም የተለየ የ Gemini App መልቀቁን ገልጿል። ይህም Google ከዚህ ቀደም በ Browser ላይ ብቻ የነበሩ አገልግሎቶቹን ወደ Desktop Ecosystem በስፋት እያመጣ መሆኑን ያሳያል።
መተግበሪያውን እንዴት ልጠቀመው?
በመጀመሪያ፣ መተግበሪያውን ያውርዱ
ካወረዱት በኋላ፣ መተግበሪያው ከሚገኝበት ፎልደር በመሄድ መተግበሪያውን ወደ ኮምፒውተርዎ ይጫኑ።
አፕሊኬሽኑ የሚጫነው በኢንተርኔት ኮኔክሽን ስለሆነ ኮምፒውተሩ ከኢንተርኔት ጋር መገናኘት አለበት።
የመጫኑ ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ መተግበሪያው ወደ ጉግል አካውንትዎ እንድትገቡ የሚያደርግ interface ያመጣል። እዚህ ላይ ሁለት ምርጫዎች አሉ። አፕሊኬሽኑን ያለአካውንት መጠቀም ቢችሉም፣ በአካውንትዎ ገብተው መጠቀም ቢጀምሩ የተሻለ አገልግሎት ያገኛሉ።
የሴታፕ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መተግበሪያውን ለመክፈት Alt+ Space ይጠቀሙ።
አሁኑኑ አዲሱን የ Google App ለ Windows በመጫን የ Search እና የ AI ልምድዎን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ይችላሉ።
Leave a Reply