G Tech Ethiopia – Blog

New Jieshuo Extenssion release: Use Ultimate Downloader

Ultimate Downloader: ለ Jieshuo ተጠቃሚዎች የቀረበ እጅግ ዘመናዊ የሚዲያ ማውረጃ Extension!

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ለ Jieshuo Screen Reader ተጠቃሚዎች እጅግ አስደሳች እና ጠቃሚ Extenssion ይዘንላችሁ መጥተናል።

A.K Mods አዲስ እና ሁሉንም በአንድ የያዘ Ultimate Downloader የተባለ Extension በይፋ ለቀዋል።

Join our Telegram Channel
ይህ Extension የሚዲያ ፋይሎችን ከማውረድ ባለፈ፡ የወረዱ ፋይሎችን ለማስተዳደር እና በቀጥታ ለማጫወት የሚያስችሉ እጅግ የረቀቁ Features ተካተውበታል።

አልትሜት ዳውንሎደርን ያውርዱ

አልቲሜት ዳውንሎደርን ለማውረድ፣ ይሄንን ይጫኑ

የ Ultimate Downloader ዋና ዋና Features

  • Multi-Platform Support: አንድ ወጥ የሆነ Interface በመጠቀም ከ Instagram፣ Facebook፣ YouTube እና Spotify ላይ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሚዲያዎች ያለምንም እንግልት ማውረድ ያስችላል።
  • Format and Quality Selection: ለ Facebook ቪዲዮዎች HD እና SD ጥራቶችን መምረጥ የሚቻል ሲሆን፣ ለ YouTube ደግሞ የተለያዩ የ Video resolutions እና Audio-only ፋይሎችን እንደ ፍላጎታችሁ መምረጥ ትችላላችሁ።
  • Smart Download Engine: ኤክስቴንሽኑ ጠንካራ የሆነ Download manager ያለው ሲሆን፣ በ Background notifications እና በ Automatic internal fallback ሲስተም የታገዘ ነው። ይህም ማውረድ የጀመራችሁት ፋይል ሳይቋረጥ እንዲጠናቀቅ ይረዳል።
  • Dedicated History Manager: በ More Options ሜኑ ውስጥ ለእያንዳንዱ Platform (Instagram, Facebook, YouTube, Spotify) ተለይተው የተቀመጡ Download histories በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።
  • YouTube History Filter: በ YouTube History list የሚገኙትን ፋይሎች የ Toggle switch በመጠቀም Video ብቻ ወይም Audio ብቻ ለይቶ ማየት ይቻላል።
  • Multi-Select Operations በ History ዝርዝር ውስጥ ያለን ማንኛውንም ፋይል Long-press በማድረግ Multi-select mode በመግባት ብዙ ፋይሎችን በአንድ ጊዜ Share ለማድረግ ወይም Delete ለማድረግ ይመቻል።
  • Detailed File Information ስለ ፋይሉ ዝርዝር መረጃዎችን ማለትም ትክክለኛ የፋይል ስም Format type፣ መጠን (Size in MB)፣ የወረደበት ቀን እና የተቀመጠበትን ቦታ (Storage location) በአንድ Interface ማወቅ ይቻላል።
  • Immersive Media Player: መተግበሪያው በውስጡ Integrated media player የተካተተለት ሲሆን፡ እንደ Play፣ Pause፣ Fast Forward፣ Rewind እና በቀላሉ በፋይሎች መካከል የመቀያየር (Next/Previous) በተኖችን ይዟል።

ኤክስቴንሽኑን እንዴት አድርጌ ልጠቀመው?

መጀመሪያ፣ ፋይሉን አውርዱትና ወደ Jieshuo+ Import ያድርጉት።

Import ከተደረገ በኋላ፣ Jieshuo Menu በመግባትና Extenssions ከሚለው በመግባት፣ ከሚመጡት ኤክስቴንሽኖች መካከል Ultimate Downloader የሚለውን በመንካት ኤክስቴንሽኑን ይክፈቱት።

ከዚያም፣ ከመጣው EditBox ለማውረድ የፈለጉትን የቪዲዮ ሊንክ ያስገቡለት።

ከዚያም፣ Start Download የሚለውን በመንካት፣ የሚፈልጉትን ቪዲዮ ማውረድ ይችላሉ።

ኤክስቴንሽኑ ፋይል ማውረድ ከመጀመሩ በፊት የፋይል ታይፕና ኳሊቲ ያስመርጣል፤ ስለዚህ ከመረጣቹህለት በኋላ ነው ማውረድ የሚጀምረው።

ፋይሉ ከወረደ በኋላ፣ ኤክስቴንሽኑ ፋይሉ መውረዱን ይነግራቹህና፣ ፋይሉን እንድታጫውቱት የሚያደርግ ኢንተርፌስ ወዲያውኑ ያመጣል።

ፋይሉን ለማግኘት፣ ከስልካቹህ Download ፎልደር ውስጥ ግቡ።

ለ Jieshuo ተጠቃሚዎች ይህ Extension ስራን በእጅጉ የሚያቀላጥፍ እና የግድ ሊኖራቸው የሚገባ extenssion ነው። አሁኑኑ ጭናችሁ በመጠቀም ለውጡን ይመልከቱ!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

1
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *