G Tech Ethiopia – Blog

Intro to device and app info: (Useful Jieshuo+ Extenssion for Jieshuo users)

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ለ Jieshuo + Screen Reader ተጠቃሚዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ Extension ይዘንላችሁ መጥተናል።

የዚህ Extension ስም Device and App info ሲሆን፣ ስለ ስልካችሁ Hardware እና ስለጫናቹሃቸው Applications ጥልቅ መረጃዎችን በአንድ ቦታ ይሰጣል።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

Download Device and app extenssion

ኤክስቴንሽኑን ለማውረድ ይሄንን ይጫኑ

ይህ Extension ከመከፈቱ በፊት ተከፍቶ የነበረውን Application በሚመለከት በርካታ ዝርዝር መረጃዎችን ያቀርባል። ከነዚህም መካከል:

  • Application package name
  • Version numbers
  • እንዲሁም አፑ System application ይሁን ወይም እናንተ የጫናችሁት መሆኑን ይነግራችኋል።

በተጨማሪም የ Application category (ለምሳሌ Productivity, Video, Audio), አፑ የተጫነበት ቀን እና ለመጨረሻ ጊዜ Update የተደረገበትን ቀን በዝርዝር ያሳያል።

አፑን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስፈልገውን የ Android version ጭምር ማወቅ ይቻላል።

ስለ ስልካችሁ ጠቅላላ ዝርዝር መረጃ ማወቅ ከፈለጋችሁ፣ ኤክስቴንሽኑ በቀጥታ ከ GSM Arena Website መረጃዎችን ያገኛል።። ይህንን መረጃ ለማግኘት ግን ስልካችሁ Internet ሊኖረው ይገባል።

በኤክስቴንሽኑ ውስጥ በምታገኙት ማንኛውም መረጃ ላይ Click በማድረግ ያንን መረጃ በቀጥታ ወደ Android clipboard ኮፒ ማድረግ ትችላላችሁ። ይህ ኮፒ የሚያደርገው በ Android ሲስተም Clipboard እንጂ በ Jieshuo Clipboard አለመሆኑን ልብ ይበሉ።

አፕሊኬሽኑ በ Google Play Store ላይ የ Beta program ካለው፣ በዚህ Extension አማካኝነት በቀላሉ Beta ቨርዥኑን መቀላቀል ትችላላችሁ። እንዲሁም አፑን እንደ Samsung Galaxy Store ባሉ ሌሎች አፕሊኬሽን ማውረጃ ውስጥ የመፈለግ አማራጭ አለው።

Internet የሚያስፈልጋቸው እንደ Phone specifications እና Beta joining ያሉ ስራዎችን ስትሰሩ Internet ከሌለ፣ ኤክስቴንሽኑ በራሱ መልዕክት ያሳያችኋል። በዚያው ቅጽበት የ Wi-Fi ወይም Mobile data settings ለመክፈት የሚያስችሉ Buttons እዚያው ላይ ስለሚገኙ ስራችሁን ያቀላጥፍላችኋል።

ይህ Extension ስለ ስልካቸው እና ስለሚጠቀሙባቸው አፖች ዝርዝር መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ የ Jieshuo ተጠቃሚዎች የግድ ሊኖራቸው የሚገባ ኤክስቴንሽን ነው!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *