ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ የ YouTube ቪዲዮዎችን እና ኦዲዮዎችን በቀላሉ ማውረድ ለምትፈልጉ ተጠቃሚዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ AbsoluteYoutube የተባለ አዲስ NVDA add-on ይዘንላችሁ ቀርበናል።
AbsoluteYoutube የ YouTube ቪዲዮዎችን እና media ፋይሎችን በቀጥታ ከ browser ላይ በ MP3, MP4, ወይም WAV formats ለማውረድ የሚያስችል አስፈላጊ የሆነ NVDA add-on ነው።
ይህ add-on ሙሉ በሙሉ ዳውንሎድ ያልሆኑ ፋይሎችን ከቆሙበት ለመቀጠል፣ ቪዲዮዎችን trim ለማድረግ፣ snapshots ለመውሰድ፣ አጫጭር URL ኮፒ ለማድረግ እና failed የሆኑ ፋይሎችን manage ለማድረግ የሚያስችል smart background systems ያካተተ ነው።
እነዚህን ሁሉ አገልግሎቶች ደግሞ ሾርት ከት ቁልፎችን እና menus በመጠቀም ማግኘት ይቻላል።
Listen to this article
Loading voices…
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload AbsoluteYoutube-v2026.8.0
AbsoluteYoutubeን ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑዋና ዋና Short cut keys
- Insert +Y download ለማድረግ የሚያገለግል ቁልፍ ሲሆን፣ እንደሚከተለው መጠቀም እንችላለን።
- አንድ ጊዜ ሲጫን፣ በጥራት MP3 ለማውረድ ያስችላል።
- ሁለት ጊዜ ሲጫን፣ MP4 ቪዲዮ ለማውረድ ይጠቅማል።
- ሶስት ጊዜ ስንጫን፣ በ.wav ፋይሉ ዳውንሎድ ማድረግ እንችላለን።
- Options and tools: Control + Shift + Y
- አንድ ጊዜ ሲጫን፣ ሁሉንም ቱሎች ለማግኘት context menu ይከፍታል።
- ሁለት ጊዜ ሲጫን፣ የወረዱ ፋይሎች የሚቀመጡበትን destination folder ይከፍታል።
- ሶስት ጊዜ ሲጫን፣ Unbound Search ለማድረግ የሚያስችለውን New Search Dialog ይከፍታል።
- Insert+Ctrl+Y በማድረግ Auto-Download ማብራት እና ማጥፋት ይቻላል።
- Insert+Shift+Y የ playlist mode ምርጫን ለማብራት ወይም ለማጥፋት ያገለግላል።
- ALT+Windows+Y የ MP3 qualityን ለመቀያየር ይረዳል (128, 192, 256, እና 320 kbps)።
- YouTube ላይ በመግባት የምትፈልጉትን channel URL ኮፒ ማድረግ።
- የAbsoluteYoutube Context Menu በመክፈት Favorite Channels የሚለውን መምረጥ።
- አዲስ channel add ለማድረግ የሚሰጠውን ምርጫ በመምረጥ ኮፒ ያደረጋችሁትን URL paste ማድረግ።
- ከ context menu ውስጥ Trim setting መክፈት።
- ከዚያም ቪዲዮው የሚጀምርበትን እና የሚያልቅበትን ጊዜ እንዲሁም የምትፈልጉትን format መምረጥ።
ይህ ሾርት ከት በ instant download እና በ Queue Mode መካከል ለመቀያየር ያገለግላል።
ይህ ምርጫ ሲጠፋ ፋይሎች በፈለግነው ጊዜ እንዲወርዱ ወደ Download List Manager ይላካሉ።
እነዚህን ቁልፎች በ NVDA Input Gestures ውስጥ ገብቶ እንደ አዲስ ማስተካከል ይቻላል።
የዋና ዋና አገልግሎቶች ማብራሪያ
Unbound Search Dialog
ይህ እንደተለመደው አይነት ፍለጋ አይደለም። ሶስት ጊዜ Shift+Ctrl+Y በመጫን የተለየ የፍለጋ በይነገጽ ውስጥ መግባት ያስችላል። የ YouTube ድረገጽ በ history ላይ ተመስርቶ ፍለጋዎችን እንደሚገድበው ሳይሆን፣ ይህ tool የተለያዩ raw data በማምጣት በሌላ ጊዜ ሊታዩ የማይችሉ በርካታ ቪዲዮዎችን እና መረጃዎችን እንድታገኙ ያደርጋል።
Favorite Channel Collection
የምትወዷቸው creators የሚለቋቸውን አዳዲስ ቪዲዮዎች እንዳያመልጣችሁ ይህ አገልግሎት ይረዳል። የእናንተን collection ለማዘጋጀት የሚከተሉትን ደረጃዎች ተጠቀሙ።
የዚህ አገልግሎት ጥቅም፣ አንዴ channel add ካደረጋችሁ በኋላ በማንኛውም ጊዜ ይህንን channel በ dialog በኩል ስትከፍቱ አዳዲስ የተጫኑ ቪዲዮዎችን በራሱ ጊዜ ቼክ በማድረግ ወዲያውኑ በ list መልክ ያቀርብላችኋል።
Download List Manager እና Smart Queue
በአንዴ ብዙ ቪዲዮ እንዲያወርድ አዶኑን አዛችሁት ከሆነ እና የታዘዙት ቪዲዮዎች እስከሚወርዱ ጊዜ አጥታቹህ ወይም ስራ በዝቶባችሁ ወዲያውኑ ማውረድ ካልፈለጋችሁ NVDA+Ctrl+Y በመጫን Auto-Download ማጥፋት ትችላላችሁ።
በዚህ ጊዜ ማውረድ የፈለጋችኋቸው ፋይሎች በሙሉ ወደ Queue ይላካሉ።
እነዚህን ፋይሎች እንደገና ለማውረድ ከ Context Menu ውስጥ Download List Manager መክፈት ያስፈልጋል።
እንዲሁም፣ በማንኛውም ፋይል ላይ Right-click በማድረግ ወይም Shift + F 10 ወይም Applications በመንካት ማውረድ መጀመር፣ ማጥፋት፣ ወይም እንደገና መሞከር ይቻላል።
Smart Background Download System
Queue Manager: ፋይሎች አንድ በአንድ እንዲወርዱ በማድረግ CPU እና RAM ይቆጥባል።
Resume on Restart: ለማውረድ የፈለግነው ፋይል ዳውንሎድ ተደርገው ሳይጨርሱ የሆነ ችግር ቢፈጠር፣ በጊዜያዊነት save ተደርገው NVDA ዳግም ሲከፈት በራሱ ጊዜ ማውረድ ይቀጥላል።
Trim Video Clips
ይህ አገልግሎት፣ ሙሉውን የYouTube Video ለማውረድ የማትፈልጉ ቢሆንና የተወሰነው የቪዲዮው ክፍል ለማውረድ ፍላጎታቹህ ቢሆን፣ የሚከተለውን አድርጉ።
Download Fail Manager
ያልወረዱ እና failed የሆኑ ፋይሎችን ዝርዝር ይይዛል። በማንኛውም ፋይል ላይ Right-click በማድረግ እንደገና መሞከር፣ ማጥፋት ወይም ቀሪ ፋይሎችን በሙሉ ማውረድ ይቻላል።
ማሳሰቢያ: ሁሉም አገልግሎቶች በ NVDA Settings ውስጥ Absolute YouTube በመግባት እንደ ፍላጎታችሁ ማስተካከል ይቻላል።
Leave a Reply