ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ ለ NVDA ተጠቃሚዎች እጅግ ጠቃሚ የሆነ፣ በተለይም Internet ላይ ጊዜያቸውን ለሚያሳልፉ ሰዎች ስራን የሚያቀል አዲስ Add-on ይዘንላችሁ ቀርበናል። ይህ Add-on “AbsoluteSite” ይባላል።
በInternet ላይ መረጃዎችን ስንፈልግ፣ የትኛው Website ላይ እንዳለን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። አንዳንዴም የገባንበትን ገጽ URL በፍጥነት ለማወቅ ወይም ለሌሎች ለማጋራት እንፈልጋለን። ይሄን ለማድረግ በተለምዶ አድሬስ ባሩን ፈልጎ ከዚያ ላይ የተጻፈውን URL ኮፒ ማድረግ ይጠበቅብናል፤ ይህ ደግሞ ጊዜ ሊወስድ እና አሰልቺ ሊሆን ይችላል። AbsoluteSite የተፈጠረው ይሄንን ችግር ለመፍታት ነው!
Listen to this article
Loading voices…
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelDownload AbsoluteSite
AbsoluteSiteን ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ።የዚህ አዶን ጥቅሞች
AbsoluteSite የተባለውን የ NVDA Addon ጭኖ መጠቀም፣ ወደምትወዷቸው ወይም በተደጋጋሚ የምትጠቀሙባቸውን ዌብሳይቶች በፍጥነት ለመክፈት የሚያስችል አስፈላጊ የሆነ tool ነው።
ረዣዥም URLs ከመጻፍ ወይም bookmarks ውስጥ ገብቶ ከመፈለግ ይልቅ ማንኛውንም ገጽ በካታጎሪ፣ በፈለግነው ስም ሴቭ በማድረግ እና በፈለግነው ጊዜ በመክፈት፣ የዌብሳይት አጠቃቀማችንን ማሻሻል የሚያስችል አዶን ነው።
Key Features
- Site Manager: በ custom categories የተቀመጡ እና save ያደረጋችኋቸውን links በሙሉ ለመክፈት ያገለግላል።
- Smart Capture: አንድን shortcut key ሁለት ጊዜ በመጫን የከፈታችሁትን ገጽ save ለማድረግ ያስችላል።
- Most Visited: በብዛት የምትጠቀሙባቸውን ገጾች በራሱ ጊዜ track በማድረግ የምትወዷቸውን ዌብሳይቶች መርጣችሁ pin ለማድረግ ያስችላል።
- Quick Search: ማናቸውንም የተጫኑ browser በመጠቀም የምትፈልጉትን ጽፋችሁ በፍጥነት Google ላይ search ለማድረግ ይጠቅማል።
- Full Control: የተቀመጡትን ገጾች rename ማድረግ፣ reorder ማድረግ፣ move ማድረግ ወይም pin ማድረግ ይቻላል።
- ሁሉም አገልግሎቶች በ keyboard እና በ context menus በኩል ነው የሚሰሩት።
- Local Storage: ሁሉም መረጃዎች በራሳቹህ ኮምፒውተር ላይ የሚቀመጡ ሲሆን፣ የዌብሳይት አጠቃቀም ታሪካቹህ ኢንተርኔት ላይ ሼር አይደረግባችሁም።
How to Use
- በመጀመሪያ፣ ብዙ ጊዜ የምትጠቀሙበትን ዌብሳይት በፈለጋችሁት ብራውዘር ክፈቱት።
- ዌብሳይቱ እንደከፈተ ወደአዶኑ ሴቭ እንዲሆንላቹህ ከፈለጋቹህ፣ Alt + Back space ሁለት ጊዜ በፍጥነት ተጫኑ።
- የዌብሳይቱን ስም፣
- የዌብሳይቱን ሊንክ፣
- የዌብሳይቱን ካታጎሪ ያሳያል።
- ሴቭ የተደረጉ ዌብሳይቶችን ለማግኘት፣ Alt + Back Space አንድ ጊዜ ተጫኑ።
- ብራውዘራችሁን ተጠቅማቹህ የምትፈልጉትን ጉግል ላይ ሰርች ለማድረግ፣ Alt + Windows + Back Space አንዴ ስትጫኑ፣ መፈለጊያው ይከፈትላቹሀል።
- በተደጋጋሚ የከፈታችሁት ዌብሳይት ማን እንደሆነ ለማወቅ፣ Alt + Back Space ሶስት ጊዜ በፍጥነት ተጫኑ።
ከዚያም፣ አዶኑ ይከፈትና፣
ሁሉንም ኤዲት ማድረግ የምትችሉ ሲሆን፣ አንድን ዌብሳይት ሴቭ ከማድረጋቹህ በፊት የዌብሳይት ካታጎሪ ካልፈጠራቹህ በመጀመሪያ መፍጠሩ አስፈላጊ ነው።
Leave a Reply