በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ G Tech Ethiopia አዲስ ነገር ፖስት ስናደርግ ማስታወቂያ እንዲደርስዎት ይፈልጋሉ? አዎ፣ እፈልጋለሁ አይ፣ አመሰግናለሁ።

G Tech Ethiopia – Blog

Productivity Companion: All-in-One Productivity Workspace

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ለአብዛኞቹ የዕለት ተዕለት ስራዎቻችን ወሳኝ የሆነ አንድ ድንቅ መተግበሪያ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

ይህ መተግበሪያ Productivity Companion ይሰኛል። በቅርቡ አዲስ ማሻሻያ በማድረግ V4.0.1 ላይ የደረሰ ሲሆን፣ All in One Productivity Workspace በመሆን የተለያዩ ጠቃሚ መገልገያዎችን በአንድ ላይ የያዘ አስፈላጊ ሶፍትዌር ሆኗል።

አፕሊኬሽኑ ለ conversion እና ለሌሎችም በርካታ አገልግሎቶች ስለሚጠቅም ለማንኛውም ሰው እጅግ አስፈላጊ ነው። ዋና ዋና አዳዲስ እና የተሻሻሉ አገልግሎቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል

follow us on telegram

Join our Telegram Channel

Download Productivity Companion

Productivity Companion የተባለውን ሶፍትዌር ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ።

Features of Productivity Companion

Audio to Video Converter:

የኦዲዮ ፋይልን ወደ ቪዲዮ ለመቀየር እና ምስል ጨምሮ የተለያዩ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ያስችላል።

Audio Transcriber:

የተለያዩ transcription models በመጠቀም የኦዲዮ ፋይሎችን ወደ ጽሁፍ ይቀይራል።

Currency Converter:

የገንዘብ ምንዛሬዎችን ወቅታዊ በሆነው የምንዛሬ ተመን መሰረት በፍጥነት ወደ ተለያዩ ሀገራት ገንዘብ convert ለማድረግ ያስችላል።

Document Reader:

PDF እና PPTX እንዲሁም EPUB እና DOCX ፋይሎችን ለማንበብ የሚያስችል ሲሆን text to speech እና PDF cryptography እንዲሁም PDF OCR አገልግሎቶችን አካቷል።

HTML to Markdown Converter:

Pandoc በመጠቀም የ HTML ዶክመንቶችን ወደ Markdown ፎርማት convert ያደርጋል።

Markdown to HTML Converter:

የ Markdown ዶክመንቶችን ወደ HTML ፎርማት ይቀይራል።

Image OCR:

Tesseract OCR በመጠቀም ከማንኛውም ምስል ላይ ጽሁፎችን extract ያደርጋል።

Image Resizer:

ፎቶዎችን ወደ አነስተኛ መጠን resize ያደርጋል። ይህ ደግሞ በተለይ ኦንላይን ፎርሞችን ለመሙላት በጣም ጠቃሚ ነው።

Notes Manager:

የተለያዩ ማስታወሻዎችን create, edit, organize, import እና export ለማድረግ ያገለግላል።

PDF to Image Converter:

የ PDF ፋይሎችን ወደ ምስሎች convert አድርጎ ለማስቀመጥ ያስችላል።

Text to Speech:

Google Text to Speech እና Microsoft natural voices በመጠቀም ጽሁፎችን ወደ ኦዲዮ convert ያደርጋል እንዲሁም ኦዲዮውን save ማድረግ ይቻላል።

Text to Image Converter:

ከጽሁፍ ላይ ምስሎችን ለመፍጠር እና ሎጎዎችን፣ ቀለሞችን እና ፎንቶችን ለመጨመር ያስችላል።

Text Translator:

ጽሁፎችን ወደተለያዩ ቋንቋዎች በፍጥነት እና በትክክል ይተረጉማል።

Video to Audio Converter:

የቪዲዮ ፋይልን ወደ ኦዲዮ የሚቀይር ሲሆን፣ በ batch መልክ በርካታ ቪዲዮዎችን በአንድ ጊዜ መቀየር ይችላል።

Voice Recorder:

ድምጽን ለመቅረጽ፣ ማቋረጥ እና መቀጠል የሚያስችሉ አማራጮችን የያዘ የድምጽ መቅረጫ ነው።

Weather Information:

የከተማ ስም በማስገባት የ weather ሁኔታን ማየት ያስችላል።

Wikipedia Search:

መረጃዎችን በፍጥነት ለመፈለግ በቀጥታ Wikipedia ላይ ፍለጋ ለማድረግ ይጠቅማል።

Word to EPUB Converter:

የ Microsoft Word ፋይልን ፎርማቱን ሳይለቅ ወደ EPUB ዶክመንት convert ያደርጋል።


የዚህ መተግበሪያ አንዱ እና ትልቁ ልዩ ባህሪ ሙሉ በሙሉ accessible መሆኑ ነው።

በአብዛኛው ጊዜ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ፎቶዎቻችንን ወይም ዶክመንቶቻችንን በኢንተርኔት ላይ upload ማድረግ ይጠበቅብናል። ይህ ደግሞ ለአንዳንድ ሰዎች የ privacy ስጋት ሊፈጥር ይችላል። የ Productivity Companion አብዛኛዎቹ አገልግሎቶች ግን ሙሉ በሙሉ offline ነው የሚሰሩት።

አፕሊኬሽኑን አውርዳችሁ በመጠቀም ስራዎቻችሁን በቀላሉ እና በፍጥነት አከናውኑ።

Happy learning, happy accessibility, happy development.

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *



error: This Content is protected !!