ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ቴሌግራም በሀምሌ ወር ለተጠቃሚዎቹ ያወጣውን አዳዲስ ማሻሻያዎችን ለማስተዋወቅ ፈልገናል።
በዚህ አዲስ Update አማካኝነት መተግበሪያው የሚኖረው አገልግሎት ይበልጥ የላቀ እና ለአጠቃቀም ምቹ ሆኗል።
follow us on telegram
Join our Telegram ChannelRich Text Editor
በአዲሱ ማሻሻያ ላይ የተጨመረው የ Rich Text Editor አገልግሎት ተጠቃሚዎች ረጅም ጽሁፎችን፣ ብሎጎችን እና አርቲክሎችን በቀላሉ እንድንጽፍ ያስችላል።
በዚህ አገልግሎት ውስጥ የሚከተሉትን ማድረግ ይቻላል፦
- ለተለያዩ ጽሁፎች የተለያዩ የጽሁፍ ፎርማቶችን መስጠት እና Headings, Tables, Lists, Quotes እንዲሁም Code blocks መጨመር።
- ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን በቀጥታ በጽሁፉ መካከል ማስገባት።
- የCocoon tools በመጠቀም ሙሉ ግላዊነትን የጠበቀ ጽሁፍ፣ የሂሳብ ቀመሮችን ወይም ሠንጠረዦችን መስራት።
- በአንድ ጊዜ ውስጥ እስከ 32,768 ፊደላትን የያዘ መልዕክትን መላክ።
ይህ አገልግሎት አሁን ላይ ለ Telegram Premium ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረበ ነው።
Communities
በርካታ ተዛማጅነት ያላቸው ቻናሎችን፣ ግሩፖችን እና ቦቶችን በአንድ ላይ በማገናኘት የተደራጀ ማዕከል መፍጠር የሚያስችል አዲስ ገጽታ ነው። ተጠቃሚዎች ያለ መጋበዣ ሊንክ በቀላሉ መቀላቀል ይችላሉ። ግሩፖች በ Visible ወይም Hidden ሁኔታ እንዲቀመጡ ማድረግ ይቻላል።
Ephemeral Messages በግሩፖች ውስጥ
ቦቶች የሚልኳቸው መልዕክቶች ግሩፑን እንዳያጨናንቁ የሚያደርግ አዲስ መንገድ ተፈጥሯል። አሁን ላይ ቦቶች የሚልኳቸው እንደ ሰላምታ፣ ግላዊ የ AI ማጠቃለያዎች እና የድጋፍ መልዕክቶች ለግለሰቡ ብቻ የሚታዩ ይሆናሉ።
የተሻሻለ የ GIF ፍለጋ
በ GIF ፓናል ውስጥ ከ 350 ሚሊዮን በላይ የሆኑ ፋይሎችን በ 36 ቋንቋዎች በፍጥነት መፈለግ የሚቻል ሲሆን፣ ፍለጋው ከማንኛውም ሶስተኛ ወገን ነፃ እና ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው።
ይህ አዲስ ማሻሻያ የቴሌግራምን አጠቃቀም ፍጹም የተለየ ደረጃ ላይ ያደርሰዋል!
Leave a Reply