በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ G Tech Ethiopia አዲስ ነገር ፖስት ስናደርግ ማስታወቂያ እንዲደርስዎት ይፈልጋሉ? አዎ፣ እፈልጋለሁ አይ፣ አመሰግናለሁ።

G Tech Ethiopia – Blog

Beyond the Play Store: A Guide to Advanced Android Customization

Written by

in

ሰላም! ዛሬ አንድን አፕሊኬሽን ፕለይ ስቶር ላይ ባትጭኑትም፣ ስልካቹህ ያንን አፕ ፕለይ ስቶር ላይ እንደጫናችሁት እንዲያስብ እንዴት እንደምታደርጉ እናያለን።

እንደምታውቁት፣ ፕለይ ስቶር በጉግል የተሰራ ለአንድሮይድ ስልኮቻችን ሶፍትዌር ለማውረድ ህጋዊ ፕላትፎርም ነው።

ታዲያ ጉግልም ሆነ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች አፕሊኬሽኖችን ከፕለይ ስቶር እንድንጭን ይመክሩናል። በእርግጥ፣ ከፕለይ ስቶር የሚመጡ አፕሊኬሽኖች የጉግልን ጥብቅ የሴኪውሪቲ ፍተሻዎችን አልፈው ስለሆነ ፐብሊሽ የሚደረጉት፣ ከደህንነት አንጻር አፕሊኬሽኖችን ከዚያው ከፕለይ ስቶር መጫን ልክ ሊሆን ይችላል።

አንዳንዴ ደግሞ ኩባንያዎች መተግበሪያዎችን ሲያበለጽጉ፣ ስልኮቻችን ላይ የሚገኙ መተግበሪያዎች ከፕለይ ስቶር ብቻ መጫናቸውን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ።

ይህንን ጽሁፍ በጥንቃቄ በማንበብና በመተግበር፣ አንድን አፕሊኬሽንን ከፕለይ ስቶር ሳይጫን ስልካችን ከፕለይ ስቶር እንደተጫነ እንዲቆጥረው እንዴት እንደምናደርገው እናያለን።

follow us on telegram

Join our Telegram Channel

ስልካችን ላይ የምናደርገው ተግባር

  1. በመጀመሪያ፣ ስልካችን ላይ Developer option እናበራለን።
    • ይህንን ለማድረግ፣ Settings, About phone, Software Information በቅደም ተከተል እንገባለን።
    • ከዚያም፣ Build Number የሚለውን 7 ጊዜ በፍጥነት እንጫናለን።
    • ቀጥሎ ስልካችን Screen lock ወይም Password | Pin ካለው እንድናስገባ ይጠይቀናል፤ ካስገባን በኋላ Developer option on እንደተደረገ ስልካችን ይነግረናል።
  2. ከዚያም አንዴ back ብለን ወደ ቀኝ ስንሄድ፣ “Developer option” የሚል አዲስ button እናገኛለን። ከዚያም ውስጥ እንገባና፣ USB Debugging የሚለውን ፈልገን On እናደርጋለን።
  3. ከዚያም፣ ስልካችንን ከኮምፒውተራችን ጋር በኬብል እናገናኛለን።
  4. ስልካችን Notification ላይ በመሄድ፣ “USB for File transfer” ከሚለው ውስጥ በመግባት፣ “MIDI” የሚለውን እንነካለን።
  5. ከዚያም፣ የጉግል ምርት የሆነውን ADB እናወርዳለን።
  6. የጉግል ምርት የሆነውን ADB ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ

    የወረደውን ፋይል በዊንራር ወይም በሌላ አርካይቨር ፋይሉን ኤክስትራክት ማድረግ ይጠበቅብናል።

  7. ከዚያም፣ ኤክስትራክት ከተደረገው ፋይል ላይ ሆነን “Alt + D” እንነካና፣ አድሬስ ባሩ ሲከፈትልን፣ ከአድሬሱ መጀመሪያ ላይ ከርሰራችንን በኮንትሮል ሆም በማድረግ፣ CMD ብለን ጽፈን Space አድርገን፣ ኢንተርን እንጫናለን።
  8. አሁን የሚቀረን ስልካችን ፕለይ ስቶር እንደተጫነ እንዲቆጥርልን የምንፈልገውን አፕሊኬሽን ወደ ስልካችን በኮምፒውተራችን መጫን ነው። ይህንን ለማድረግ በመጀመሪያ የስልኩን አፕሊኬሽን ከኮምፒውተራችን ማውረድ ግዴታችን ነው።

  9. ይህንን ኮማንድ በጥንቃቄ ያስገቡ።
  10. adb install -r -i “com.android.vending” “C:\path\to\your\app.apk”

    ያስታውሱ! “C:\path\to\your\app.apk” የሚለው የኮማንዱ ክፍል ለምሳሌ የተጻፈ ነው፤ በዚህ ምትክ የራሳችሁን የስልክ አፕሊኬሽን ፋይል ትክክለኛ መገኛ ማስገባት ይኖርባቹሃል።

    እንዴት የስልኩ አፕሊኬሽን መገኛን ለኮምፒውተራችን እንንገረው?

    • ወደ ስልኩ አፕሊኬሽን ፋይል ይሂዱ፤ ፋይሉ ላይ ትሆኑና ኮንትሮል ሺፍት ሲን በአንድላይ ስትጫኑ የስልኩ ትክክለኛ መገኛ ወደክሊፕቦርዱ ኮፒ ይሆናል።
    • ከዚያም ወደ ኮማንድ ፕሮምፕቱ በመሄድ ኮንትሮል እና ቪን በመንካት ከክሊፕቦርዱ የነበረውን የስልኩ አፕሊኬሽን መገኛ የያዘውን ጽሁፍ ወደኮማንድ ፕሮምፕቱ ፔስት ያደርገውና ኢንተር ስትነኩ ወደስልካቹህ አፕሊኬሽኑን ይጭነዋል።

ይህንን መመሪያ በመጠቀም፣ ማንኛውንም የስልክ አፕሊኬሽን ከፕለይ ስቶር እንደተጫነ እንዲቆጠር ማድረግ ይቻላል።

ይህ ዘዴ ስልካችሁን በነፃነት እንድትጠቀሙ ያግዛችኋል። ይህንን መረጃ ለጓደኞቻችሁ ማካፈል እንዳትረሱ! ስለ አጠቃቀሙ ያላችሁን አስተያየት በኮመንት ላይ እጠብቃችኋለሁ።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *