በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ G Tech Ethiopia አዲስ ነገር ፖስት ስናደርግ ማስታወቂያ እንዲደርስዎት ይፈልጋሉ? አዎ፣ እፈልጋለሁ አይ፣ አመሰግናለሁ።

G Tech Ethiopia – Blog

Intro to Eyeguide: Navigation and accessibility

Logo for Eyeguide

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሰዎችን ህይወት እንዴት በቀላሉ እንደሚቀይሩ የሚያሳይ አንድ ድንቅ መተግበሪያ ይዘንላችሁ መጥተናል። መተግበሪያው EyeGuide Vision ይባላል።

ይህ መተግበሪያ በተለይ ለአይነ ስውራን እና ዝቅተኛ እይታ ላላቸው ተጠቃሚዎች ተብሎ የተሰራ የ Accessibility መተግበሪያ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ያሉበትን አካባቢ ያለ ሰው ረዳት በራሳቸው እንዲረዱ እና በልበ ሙሉነት እንዲንቀሳቀሱ ይረዳቸዋል። መተግበሪያው የስልኩን ካሜራ፣ Sensors, Haptics እና በራሱ በስልኩ ላይ የሚሰራ Machine Learning በመጠቀም ነው መረጃዎችን የሚሰጠው።

Follow us on Telegram

Join Our Telegram Channel

Download Eyeguide from Google Play Store

አፕሊኬሽኑን ከፕለይ ስቶር ለማግኘት፣ ይህንን ሊንክ ይጫኑ

Features of Eyeguide

  • Real-Time Navigation Assistance፦ መተግበሪያው በአካባቢያችሁ ያሉ እንቅፋቶችን በካሜራው አማካኝነት ይለያል። ወደ አንድ ነገር እየተጠጋችሁ ስትመጡም በድምፅ እና በንዝረት ምልክት ይሰጣል። ወደ እንቅፋቱ ይበልጥ በተጠጋችሁ ቁጥር የንዝረቱ ወይም የድምፅ ማስጠንቀቂያው እየጨመረ ስለሚሄድ በሰላም ለመንቀሳቀስ ይረዳል።
  • Scene Description፦ ይህ አገልግሎት ከፊትለፊታችሁ ያለውን ሁኔታ በዝርዝር በድምፅ ይገልጽላችኋል። ለምሳሌ በአንድ ክፍል ውስጥ ስንት ወንበሮች እንዳሉ፣ ውጭ ላይ ያሉት ነገሮች ምን እንደሆኑ እና አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ ለመረዳት ይረዳል።
  • Document Reader (OCR)፦ ማንኛውንም አይነት ጽሁፎችን፣ ደብዳቤዎችን፣ ደረሰኞችን እና በመንገድ ላይ ያሉ ምልክቶችን ወደ ካሜራው በማዞር ብቻ ወዲያውኑ በድምፅ እንዲነበብላችሁ ያደርጋል። ይህ የ OCR አገልግሎት ምንም አይነት የኢንተርኔት connection አይፈልግም።
  • Currency Identification፦ የተለያዩ የገንዘብ ኖቶችን በፍጥነት እና በትክክል ለመለየት ይረዳል። ይህም ተጠቃሚዎች ግብይት ሲያደርጉ የገንዘቡን መጠን በራሳቸው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል። ነገር ግን፣ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ብርን መለየት አይችልም።
  • Color Detection፦ በአልባሳት፣ በእቃዎች ወይም በማንኛውም ቁስ ላይ ያሉ ቀለሞችን የስልኩን ካሜራ በመጠቀም በትክክል መለየት ይቻላል።

የዚህ መተግበሪያ ትልቁ ብቃት ሁሉም አገልግሎቶች 100% Offline መስራታቸው ነው። ይህም ማለት ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ሳይጠቀሙ ወይም ኮኔክሽን በሌለበት ቦታ ሁሉንም አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪም መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ በነጻ የቀረበ ነው።

EyeGuide Vision የቴክኖሎጂን አቅም ተጠቅሞ የሰዎችን ገደብ ለመቀነስ የሚሰራ ድንቅ መተግበሪያ በመሆኑ፡ ይህ መረጃ ለሚጠቅማቸው ወገኖች በማጋራት እንድታደርሱ እንመክራለን።

ስለ መተግበሪያው ያላችሁን አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

2
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *