ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ በተለይ በአዲሶቹ የ Android Versions ላይ Callለመቅዳት ለተቸገራችሁ ተጠቃሚዎች አንድ ምርጥ መፍትሄ ይዘንላችሁ መጥተናል።
እንደሚታወቀው በአሁኑ ጊዜ Google በደህንነት ምክንያት Call Recordingአስቸጋሪ አድርጎታል። ብዙዎቻችሁ ስልካችሁ ላይ የራሱ የ Call Recorder ላይኖረው ይችላል፤ ወይ ደግሞ በሌላ መተግበሪያ Call record ለማድረግ ስትፈልጉ የሌላኛው ድምጽ ላይሰማ ይችላል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ Cube ACR የተባለው መተግበሪያ እጅግ ተመራጭ ነው።
/more: For Samsung users: Record your calls with Cube ACR call recorderFollow us on Telegram
Join our Telegram Channelመጀመሪያ ወደ Galaxy Store በመግባት Cube ACR የሚለውን መተግበሪያ መጫን ይኖርባችኋል።
የሳምሰንግ አካውንት የሌላቹህ ሰዎች ደግሞ፣ ከዚህ በታች በሚገኘው ሊንክ ከዕኛ ዌብሳይት ማውረድ ትችላላቹህ።
Download Cube ACR
Cube ACRን ለማውረድ ይህንን ሊንክ ይጫኑ።መተግበሪያውን ከጫናችሁ በኋላ የሚጠይቃችሁን አስፈላጊ Permissions በሙሉ መፍቀድ አለባችሁ።
በዋናነት ደግሞ በስልካችሁ Settings ውስጥ ወደ Accessibility በመግባት ለ Cube ACR App Connector ፈቃድ መስጠት አለባችሁ። ይህ ደረጃ በጣም ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም ይህ ፈቃድ ካልተሰጠ መተግበሪያው የሁለቱንም ወገን ድምፅ በጥራት መቅዳት አይችልም።
ሁሉንም ካስተካከላችሁ በኋላ ማንኛውም ሰው ሲደውልላችሁ ወይም እናንተ ስትደውሉ መተግበሪያው በራሱ (Automatically) መቅዳት ይጀምራል። የድምፅ ጥራቱም እጅግ በጣም ግልጽ እና ለማዳመጥ አመቺ ነው።
ይህ Cube ACR መተግበሪያ ለ Samsung ተጠቃሚዎች ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም Android ስልክ የሚሆን ሲሆን በተለይ ደግሞ ለስራ ወይም ለተለያዩ አስፈላጊ መረጃዎች ጥሪዎችን መቅዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ትልቅ መፍትሄ ነው።
ይህ መረጃ ለብዙዎች ጠቃሚ ስለሚሆን ለጓደኞቻችሁ Share ማድረጋችሁን እንዳትረሱ። ስላላችሁ አጠቃቀም ወይም ያጋጠማችሁ ችግር ካለ በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን።
Leave a Reply