G Tech Ethiopia – Blog

New service from Ethio Telecom: Get new vertual number from your old Sim card

Ethio Telecom Virtual Number፡ ያለ ተጨማሪ ሲም ካርድ ሁለተኛ ቁጥር መጠቀም የሚያስችል አዲስ አገልግሎት

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ Ethio Telecom ይፋ ስላደረገው እና ብዙዎችን እያነጋገረ ስላለው Virtual Number አገልግሎት ዝርዝር መረጃ ይዘንላችሁ መጥተናል።

ይህ አገልግሎት በተለይ የግል እና የሥራ ጥሪዎችን በአንድ ስልክ ለማስተናገድ ለምትፈልጉ ፍጹም መፍትሄ ነው።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

Virtual Number ምንድን ነው?

Virtual Number ማለት ያለ ተጨማሪ SIM Card ወይም ያለ eSIM፣ ከዋናው የሞባይል ቁጥራችሁ ጋር ተያይዞ የሚሰጥ ተጨማሪ ዲጂታል ስልክ ቁጥር ነው። በአንድ ሲም ካርድ ብቻ ሁለት ቁጥሮችን እንድትጠቀሙ ያስችላችኋል።

የአገልግሎቱ ዋና ዋና መገለጫዎች

  • ተጨማሪ ሲም አያስፈልግም: ቁጥሩ ሙሉ በሙሉ ዲጂታል በመሆኑ ሌላ ሲም ካርድ መግዛት ወይም ስልክ መቀየር አያስፈልጋችሁም።
  • የቁጥር ምርጫ: ተጠቃሚዎች ባለ 9 ወይም 11 ዲጂት ቁጥሮችን መምረጥ ይችላሉ። ምንም እንኳን ወደፊት የተለያዩ መነሻዎችን (እንደ 11፣ 12፣ 13…) መምረጥ የሚቻል ቢሆንም፡ ለጊዜው ግን ከዋናው ቁጥራችሁ ጋር ተመሳሳይ መነሻ ያለው ቁጥር ነው የሚሰጠው።
  • የአገልግሎት ደረጃዎች፦: አገልግሎቱ Platinum, Gold, Silver እና Bronze የተባሉ አራት ደረጃዎች አሉት። በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊነት የቀረበው የ Silver አገልግሎት ሲሆን፣ ከዋናው ቁጥራችሁ በ 1 ዲጂት የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ቁጥር መምረጥ ትችላላችሁ።
  • Privacy: በዚህ ቁጥር ስትደውሉ ጥሪ ተቀባዩ የሚያየው የ Virtual Number ቁጥራችሁን እንጂ ዋናውን ቁጥራችሁን አይደለም። ይህም የንግድ ስራችሁን በፕሮፌሽናል መልኩ ለመምራት ይረዳል።
  • የቁጥር ብዛት: አንድ ዋና ቁጥር ያለው ተጠቃሚ ቢበዛ እስከ ሁለት Virtual Numbers መመዝገብ ይችላል።

እንዴት መጠቀም ይቻላል?

በስልካችሁ *984# ላይ በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ። ለደህንነት ሲባል ምዝገባውን ለማረጋገጥ ‘1’ን እንድትጫኑ ይጠየቃሉ።

በVirtual Number ቁጥራችሁ ለመደወል በምትፈልጉበት ጊዜ፣ ከሚደውሉለት ቁጥር በፊት “3”ን መጨመር ይኖርባችኋል። (ለምሳሌ, 0911 የሚልን ቁጥር ለመደወል፣ 30911 ብለን ጽፈን እንደውላለን ማለት ነው።)።

ሁሉም የጥሪ መዝገቦች እና የክፍያ ሂደቶች ከዋናው ቁጥራችሁ ጋር የተገናኙ ናቸው። ለመጠቀም ዋናው ቁጥራችሁ Active መሆን እና በቂ Balance ሊኖረው ይገባል።

የአገልግሎት ውል እና ስረዛ

አገልግሎቱን በየወሩ መክፈል ይኖርባችኋል። ወርሃዊ ክፍያው ካልተከፈለ አገልግሎቱ በራሱ ይቋረጣል።

ለሦስት ወራት ያህል ክፍያ ካልተፈጸመ ቁጥሩ ተመልሶ ለገበያ ይቀርባል።

አገልግሎቱን ለማቋረጥ በፈለጉ ጊዜ *984# በመጠቀም ማቋረጥ ይችላሉ። ቁጥሩ ለሦስት ወራት ተጠብቆ ይቆይላችኋል፤ ከዚያ በኋላ ግን ለሌላ ተጠቃሚ ክፍት ይሆናል።

ይህ አገልግሎት በተለይ ስልክ ቁጥራቸውን ለማያውቁት ሰው መስጠት ለማይፈልጉ እና የሥራ ጥሪዎችን ለብቻ መለየት ለሚፈልጉ ሰዎች እጅግ አመቺ ነው።

ስለ Virtual Number አገልግሎት ያላችሁን አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *