

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች!
ዛሬ ደግሞ ለ Windows 11 ተጠቃሚዎች እጅግ መልካም ዜና ይዘንላችሁ መጥተናል።
Microsoft በሚቀጥለው ግንቦት ወር ላይ ለ Windows 11 ተጠቃሚዎች እጅግ አስፈላጊ የሆነ የ Reliability Update ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
Follow us on telegram
Join Our Telegram Channelይህ ዝመና በዋናነት የሚያተኩረው ተጠቃሚዎች በዕለት ተዕለት ስራቸው ወቅት ሲያጋጥሟቸው የነበሩ የ Stability እና Performance ችግሮችን በመፍታት ላይ ነው።
ከዋና ዋናዎቹ ማሻሻያዎች መካከል ለ Taskbar የተሰጠው ትኩረት ይጠቀሳል። በብዙ ተጠቃሚዎች ዘንድ ሲስተዋል የነበረው የ Taskbar አለመረጋጋት እና Freezing በዚህ Update ሙሉ በሙሉ ይስተካከላል ተብሎ ይጠበቃል።
ሌላው ትልቅ ለውጥ በ Clipboard ላይ የተደረገው ነው። ይህም መረጃዎችን Copy እና Paste ስናደርግ የነበረውን ፍጥነት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምረዋል።
በ Storage እና Disk Management ረገድም ሰፊ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ይህም ኮምፒውተራችን ፋይሎችን በምናስተዳድርበት ወቅት ያለው Reliability ይበልጥ የተረጋጋ እንዲሆን ያደርገዋል።
በተጨማሪም ማሻሻያው በ File Explorer እና በሌሎች የሲስተሙ ክፍሎች ላይ የሚታዩ ጥቃቅን Bugs እና የ Reliability ክፍተቶችን ይደፍናል ተብሎ ይታመናል።
ተጠቃሚዎች ይህንን Update ግንቦት 2026 ላይ በ Windows Update አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።
በአጠቃላይ ይህ ማሻሻያ የ Windows 11 ተጠቃሚዎችን የኮምፒውተር አጠቃቀም ልምድ ይበልጥ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ እንደሚያደርገው እርግጠኛ ነን።
Leave a Reply