G Tech Ethiopia – Blog

Zen: New Alternative browser For Windows users

Zen Browser

Zen Browser: ከ Brave የተሻለ እና ቀለል ያለ አማራጭ ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች የቀረበ አዲስ Browser!

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ብዙዎቻችን ከምንጠቀመው Brave Browser ይልቅ ቀለል ያለ እና ዘመናዊ የሆነ አዲስ ምርጫ ይዘንላችሁ መጥተናል። ይህ አዲስ Browser Zen Browser ይባላል።

ይህ Browser የተሰራው በ Firefox Engin ላይ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ Open-source ነው። የ Zen Browser ዋና አላማ አላስፈላጊ ነገሮችን በማስወገድ እና የተጠቃሚዎችን Privacy በማስቀደም ምቹ የኢንተርኔት አጠቃቀም ልምድን መፍጠር ነው።

Follow us on telegram

Join Our Telegram Channel

ዜን ብራውዘርን ያውርዱ

ዜን ብራውዘርን ለማውረድ፣ ይሄንን ይጫኑ

ከዚህ Browser ዋና ዋና መለያዎች አንዱ የVertical Tabs አጠቃቀሙ ነው። ታቦችን ከላይ ከማስቀመጥ ይልቅ በSidebar በኩል በማድረግ ሰፊ የስክሪን ቦታ እንዲኖራችሁ ይረዳል። ይህ በተለይ ሰፊ ስክሪን ለምትወዱ ሰዎች በጣም የሚያስደስታችሁ Feature እንደሆነ እናስባለን።

Zen Mode የተባለው Feature ደግሞ ሁሉንም አላስፈላጊ የአድራሻ ሳጥኖች እና ሜኑዎችን በመደበቅ፣ ትኩረታችሁ በምታነቡት ወይም በምታዩት ነገር ላይ ብቻ እንዲሆን ያደርጋል። ይህ Feature በተለይ ትኩረት ሰብስቦ ለማንበብ ወይም ቪዲዮዎችን ለማየት በጣም ጠቃሚ ነው።

የተለያዩ ስራዎችን ለይቶ ለማስቀመጥ Workspaces የሚል አማራጭ አለው። ለምሳሌ ለስራ እና ለግል አጠቃቀም የሚሆኑ ታቦችን ለይቶ በማስቀመጥ ስራን ያቀላጥፋል።

በተጨማሪም ብራውዘሩ እጅግ ፈጣን እና ቀላል በመሆኑ፣ በኮምፒውተራችሁ ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል። እንደ Brave ያሉ Browsers በውስጣቸው የሚይዟቸው አላስፈላጊ ነገሮች የሚበዛባችሁ ከሆነ፣ Zen Browser ለእርስዎ ምርጥ አማራጭ ነው።

ይህንን አዲስ Browser አሁኑኑ ጭናችሁ በመሞከር የተለየ የኢንተርኔት አጠቃቀም ልምድ እንዲኖራችሁ እንጋብዛለን።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *