G Tech Ethiopia – Blog

What’s new on Saathi Reader V 3.8?

🚀 Saathi Reader: አዳዲስ ማሻሻያዎችን የያዘው Update በይፋ ተለቋል!

ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ በተለይ ለንባብ አፍቃሪያን እና Screen Reader ለምትጠቀሙ ተጠቃሚዎች ትልቅ እገዛ የሚያደርገውን የ Saathi Reader አዲስ ማሻሻያ ይዘንላችሁ መጥተናል።
ይህ ሶፍትዌር በ Windows ላይ መጽሐፍትን ለማንበብ የሚረዳ ሲሆን፣ አሁን ላይ ደግሞ ተጠቃሚዎችን ይበልጥ ደስ የሚል የንባብ ልምድ እንዲኖራቸው የሚያደርጉ አራት ዋና ዋና ለውጦችን አካቷል።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

Download Saathi Reader V 3.8

አዲሱን የSaathi Reader V 3.8 ያውርዱ

የመጀመሪያው ትልቅ ማሻሻያ መጽሐፍትን በ Online Synthesizer ማስደመጥ መቻሉ ነው። ለየት የሚያደርገው ደግሞ እናንተ እያነበባችሁ እያለ ገጾቹ Background ላይ process ስለሚሆኑ ያለምንም መቆራረጥ ንባባችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።

ሌላው እጅግ አስፈላጊ የሆነው ማሻሻያ የ Playback ማስተካከያው ነው። አሁን ላይ ማንበብ አቁማችሁ በሌላ ጊዜ ስትመለሱ፣ ካቆማችሁበት ትክክለኛ ቦታ ላይ ንባቡ እንዲቀጥል ተደርጎ ተስተካክሏል።

ኢንተርኔት በሌለበት ቦታ ሆናችሁ መጽሐፍትን ማድመጥ ለምትፈልጉ ደግሞ አዲሱ የ H2R Voices Feature ተጨምሯል። ይህም ተጠቃሚዎች ኦፍላይንም ሆነው ጥራት ያለው የንባብ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

በመጨረሻም የመተግበሪያው Audio Player ከበፊቱ በበለጠ Stable እንዲሆን ተደርጓል። በርካታ ጥቃቅን የሆኑ የቴክኒክ ችግሮች የተፈቱ በመሆኑ፣ አፑ ያለምንም መቆራረጥ በተሻለ ፍጥነት ይሰራል።

ይህንን ሶፍትዌር እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ ዝርዝር መረጃ ለምትፈልጉ፣ ከዚህ በፊት የለጠፍነውን የ How to use መመሪያ በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ

እነዚህ አዳዲስ ማሻሻያዎች የ Saathi Reader ተጠቃሚዎችን ፍላጎት እንደሚያሟላ ተስፋ እናደርጋለን። አሁኑኑ አፑን Update በማድረግ ለውጡን ይመልከቱ!

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

2
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *