G Tech Ethiopia – Blog

New update on Microsoft Teams (March 2026)

Microsoft Teams Logo

Microsoft በየወሩ እንደሚያደርገው ሁሉ በዚህ መጋቢት ወር ለ Microsoft Teams ተጠቃሚዎች ስራን የሚያቀላጥፉና ግንኙነትን የሚያሳልጡ አዳዲስ ማሻሻያዎችን በይፋ አቅርቧል።

እነዚህ ማሻሻያዎች በተለይ በትላልቅ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩና በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተሳታፊ ለሆኑ ተጠቃሚዎች ትልቅ ፋይዳ አላቸው።

follow us on telegram

Join our Telegram Channel

ከዋና ዋናዎቹ ለውጦች መካከል በተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በአንድ ቦታ የመቆጣጠር (Multi-tenant, multi-account) ይገኝበታል።

ተጠቃሚዎች ከአሁን በኋላ ከአንዱ ድርጅት አካውንት ወደ ሌላኛው ሳይቀያይሩ ሁሉንም መልዕክቶችና ማሳሰቢያዎች በአንድ ወጥ ገጽ ላይ መመልከት ይችላሉ።

በተጨማሪም በብዛት የሚጠቀሙባቸውን አካውንቶች Pin በማድረግ በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ይቻላል።

ሌላው አዲስ የተዋወቀው ነገር የተሻሻለው የድርጅት መዋቅር መግለጫ (Enhanced organization chart) ነው። ተጠቃሚዎች የአንድን የስራ ባልደረባ ፕሮፋይል ሲመለከቱ ግለሰቡ በድርጅቱ ውስጥ ያለውን የስራ ተዋረድ፣ የቡድኑን ስፋትና ተያያዥ መረጃዎችን በዝርዝር ማየት ይችላሉ። ይህም አዲስ ሰራተኞች ድርጅቱን በቅርበት እንዲረዱና የስራ ግንኙነቶችን እንዲያጠናክሩ ይረዳቸዋል።

በስራ ጫና ምክንያት ተጀምረው ሳይላኩ የቀሩ መልዕክቶችን ለማግኘት አሁን “Drafts quick view” የሚባል አዲስ አማራጭ ቀርቧል። ተጠቃሚዎች በተለያዩ የውይይት ክፍሎች ውስጥ የጀመሯቸውን ረቂቅ መልዕክቶች በአንድ ቦታ ተሰባስበው ማግኘት ይችላሉ። ይህም መረጃዎችን ፈልጎ ለማግኘት የሚጠፋውን ጊዜ በመቀነስ የስራ ቅልጥፍናን ይጨምራል።

በ Microsoft Teams ውስጥ ባሉት Threaded channels ላይ ደግሞ አዲስ Live meeting indicator ታክሏል። ይህም በቡድኑ ውስጥ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን ለሁሉም አባላት በግልጽ የሚያሳይ ሲሆን አባላት በቀላሉ ስብሰባውን እንዲቀላቀሉና በሃሳብ ልውውጡ ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል።

ለሲስተም አስተዳዳሪዎች ደግሞ ከውጭ ተቋማት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ቀላል የመቆጣጠሪያ መንገዶች ተዘጋጅተዋል። በ Microsoft Teams admin center ውስጥ በሚገኘው አዲስ ገጽ አማካኝነት ድርጅቶች ከውጭ ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በምን አይነት ሁኔታ መሆን እንዳለበት በግልጽና በቀላሉ መወሰን ይችላሉ።

በመጨረሻም በ Microsoft Teams በኩል የሚካሄዱ ትላልቅ ስብሰባዎችና ዝግጅቶች የፍቃድ አሰጣጥ ላይ ለውጥ ተደርጓል። ቀደም ሲል የነበሩ የላቁ የዝግጅት ማካሄጃ ብቃቶች አሁን ለሁሉም የ Microsoft Teams Enterprise ተጠቃሚዎች ክፍት እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህም ተጠቃሚዎች ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ እስከ 3,000 የሚደርሱ ታዳሚዎችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ እንዲችሉ ይረዳቸዋል።

የመረጃውን ይፋዊ ምንጭ ይመልከቱ

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *