
በWindows 11 ውስጥ የሚገኝ አንድ ቀላል ማስተካከያ የኢንተርኔት አጠቃቀማችንን ከማሻሻላችን በላይ የግል ምስጢራችን ይበልጥ የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል።
follow us on telegram
Join our Telegram Channelይህ ማስተካከያ DNS over HTTPS ወይም በአጭሩ DoH ተብሎ ይጠራል።
DNS ማለት ድረ ገጾችን በስማቸው ስንፈልግ ወደ ኮምፒውተር ቁጥር ወይም IP address የሚቀይር ሲስተም ነው።
በተለመደው ሁኔታ የዲኤንኤስ ጥያቄዎች ያለምንም Encryption ስለሚላኩ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎች ወይም ሌሎች አካላት የትኞቹን ድረ ገጾች እንደምንጎበኝ በቀላሉ ማወቅ ይችላሉ።
DNS over HTTPS ይህንን የመረጃ ልውውጥ በምስጢር ኮድ በመቆለፍ ማንም እንዳያየው ያደርጋል።
ይህ አሰራር መረጃው እንዳይሰረቅ ከመከላከል ባለፈ እንደ Google ወይም Cloudflare ያሉ ፈጣን የዲኤንኤስ አገልግሎቶችን እንድንጠቀም ስለሚያስችለን የድረ ገጾች የመከፈት ፍጥነት እንዲጨምር ያደርጋል።
ይህንን አገልግሎት በWindows 11 ላይ ለማስተካከል መጀመሪያ Settings ውስጥ በመግባት Network & internet የሚለውን መምረጥ አለብን።
በመቀጠል የምንጠቀመውን የኢንተርኔት አይነት Wi-Fi ወይም Ethernet በመጫን የDNS server assignment የሚለውን ክፍል እናገኛለን።
እዚያም Edit የሚለውን በመጫን Automatic የነበረውን ወደ Manual በመቀየር የፈለግነውን የዲኤንኤስ አድራሻ (ለምሳሌ የ Google ዲኤንኤስ 8.8.8.8) ማስገባት ይኖርብናል።
በመጨረሻም DNS encryption በሚለው ስር Encrypted only (DNS over HTTPS) የሚለውን በመምረጥ ለውጡን save ማድረግ ይቻላል።
በዚህ ቀላል መንገድ የኢንተርኔት አጠቃቀማችንን ይበልጥ ፈጣንና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ እንችላለን።
የመረጃውን ይፋዊ ምንጭ ይመልከቱ
Leave a Reply