Google በቅርቡ ተጠቃሚዎች መረጃቸውን ከሌሎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት መድረኮች በቀላሉ ወደ ራሱ እንዲያዛውሩ የሚያስችሉ አዳዲስ ማስተካከያዎችን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ስራ ላይ የዋሉት እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በተለይ ከ ChatGPT እና Claude ወደ Google Search AI ለመቀየር ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ትልቅ እፎይታን ይዘው መጥተዋል።
follow us on telegram
Join our Telegram Channel
Switching tools
ተብለው የተሰየሙት እነዚህ መገልገያዎች ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል በሌሎች ረዳቶች ላይ የነበራቸውን የግል መረጃና History ይዘው እንዲመጡ ይረዳሉ። ይህም አንድ ተጠቃሚ አዲስ ረዳት ሲጠቀም ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው የመጀመርን አድካሚ ሂደት ያስቀራል።
ከመተግበሪያዎቹ መካከል አንዱ የሆነው Import Memory
የተባለው ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች በሌሎች መድረኮች ላይ ያላቸውን የተጠቃሚነት ባህሪና ፍላጎት በቀላሉ እንዲያቀላጥፉ ይረዳል። ይህ መተግበሪያ በ
ኤአይ Prompt በመጠቀም ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል ይጠቀሙባቸው ከነበሩት እንደ
ካሉ ረዳቶች ላይ የማጠቃለያ መረጃ እንዲያመጡ ያስችላል።
ተጠቃሚዎች ይህንን ማጠቃለያ በጎግል ኤአይ Settings ገጽ ላይ በማስገባት የረዳታቸውን የማስታወስ አቅም ማሳደግ ይችላሉ።
ሌላው እጅግ አስገራሚው አማራጭImport Chat Historyየተባለው ሲሆን ይህም ተጠቃሚዎች የነበራቸውን ሙሉ የውይይት ታሪክ እስከ 5GB የሚሆን ZIP ፋይል በመጫን እንዲያዛውሩ ይፈቅዳል። በዚህም ምክንያት የነበሩ የቆዩ ውይይቶች በጎግል ኤአይ Sidebar ላይ በልዩ ምልክት ተለይተው የሚታዩ ሲሆን ተጠቃሚዎችም ካቆሙበት እንዲቀጥሉ እድል ይሰጣቸዋል።
ተጠቃሚዎች እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት Gemini ላይ በመሄድ በግራ በኩል በሚገኘው የSettings ምልክት ስር የሚገኘውን Import memory to Gemini
የሚለውን አማራጭ መምረጥ ይኖርባቸዋል። እዚያም ውስጥ የማስታወሻ ማስገቢያ ትዕዛዙንና የውይይት ማህደር መጫኛውን አማራጭ በአንድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
ጎግል ይህንን አዲስ ለውጥ ተከትሎ ቀደም ሲል Past chats
ተብሎ ይጠራ የነበረውን ክፍል ስያሜውን ወደ Memory
ቀይሮታል። ይህ ስያሜ Gemini የተጠቃሚውን የቆዩ ውይይቶችና ፍላጎቶች የማስታወስ ብቃቱን ይበልጥ እንደሚገልጽ ታምኖበታል።።
ጎግል ይህንን አገልግሎት ያለምንም ልዩነት ለነጻ ተጠቃሚዎችም ሆነ ለክፍያ ደንበኞቹ ክፍት ማድረጉ በዘርፉ ያለውን የገበያ ፉክክር ይበልጥ እእንደሚጨምረው ተገልጿል። ይህ እርምጃ ተጠቃሚዎች የፈለጉትን የኤአይ ረዳት የመምረጥ ነፃነታቸውን ከማረጋገጡም በላይ በአንድ ድርጅት ላይ ብቻ ተገድበው እንዳይቆዩ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል።
Leave a Reply