G Tech Ethiopia – Blog

Intro to Google’s Switching tools

Google በቅርቡ ተጠቃሚዎች መረጃቸውን ከሌሎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት መድረኮች በቀላሉ ወደ ራሱ እንዲያዛውሩ የሚያስችሉ አዳዲስ ማስተካከያዎችን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።

መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ስራ ላይ የዋሉት እነዚህ ቴክኖሎጂዎች በተለይ ከ ChatGPT እና Claude ወደ Google Search AI ለመቀየር ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ትልቅ እፎይታን ይዘው መጥተዋል።

follow us on telegram

Join our Telegram Channel
Claude AI

Switching tools ተብለው የተሰየሙት እነዚህ መገልገያዎች ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል በሌሎች ረዳቶች ላይ የነበራቸውን የግል መረጃና History ይዘው እንዲመጡ ይረዳሉ። ይህም አንድ ተጠቃሚ አዲስ ረዳት ሲጠቀም ሁሉንም ነገር ከመጀመሪያው የመጀመርን አድካሚ ሂደት ያስቀራል።

ከመተግበሪያዎቹ መካከል አንዱ የሆነው Import Memory የተባለው ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች በሌሎች መድረኮች ላይ ያላቸውን የተጠቃሚነት ባህሪና ፍላጎት በቀላሉ እንዲያቀላጥፉ ይረዳል። ይህ መተግበሪያ በ ጎግል ኤአይ Prompt በመጠቀም ተጠቃሚዎች ቀደም ሲል ይጠቀሙባቸው ከነበሩት እንደ ChatGPT ካሉ ረዳቶች ላይ የማጠቃለያ መረጃ እንዲያመጡ ያስችላል።

ተጠቃሚዎች ይህንን ማጠቃለያ በጎግል ኤአይ Settings ገጽ ላይ በማስገባት የረዳታቸውን የማስታወስ አቅም ማሳደግ ይችላሉ።

ሌላው እጅግ አስገራሚው አማራጭ Import Chat History የተባለው ሲሆን ይህም ተጠቃሚዎች የነበራቸውን ሙሉ የውይይት ታሪክ እስከ 5GB የሚሆን ZIP ፋይል በመጫን እንዲያዛውሩ ይፈቅዳል። በዚህም ምክንያት የነበሩ የቆዩ ውይይቶች በጎግል ኤአይ Sidebar ላይ በልዩ ምልክት ተለይተው የሚታዩ ሲሆን ተጠቃሚዎችም ካቆሙበት እንዲቀጥሉ እድል ይሰጣቸዋል።

ተጠቃሚዎች እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት Gemini ላይ በመሄድ በግራ በኩል በሚገኘው የSettings ምልክት ስር የሚገኘውን Import memory to Gemini የሚለውን አማራጭ መምረጥ ይኖርባቸዋል። እዚያም ውስጥ የማስታወሻ ማስገቢያ ትዕዛዙንና የውይይት ማህደር መጫኛውን አማራጭ በአንድ ላይ ማግኘት ይቻላል።

ጎግል ይህንን አዲስ ለውጥ ተከትሎ ቀደም ሲል Past chats ተብሎ ይጠራ የነበረውን ክፍል ስያሜውን ወደ Memory ቀይሮታል። ይህ ስያሜ Gemini የተጠቃሚውን የቆዩ ውይይቶችና ፍላጎቶች የማስታወስ ብቃቱን ይበልጥ እንደሚገልጽ ታምኖበታል።።

ጎግል ይህንን አገልግሎት ያለምንም ልዩነት ለነጻ ተጠቃሚዎችም ሆነ ለክፍያ ደንበኞቹ ክፍት ማድረጉ በዘርፉ ያለውን የገበያ ፉክክር ይበልጥ እእንደሚጨምረው ተገልጿል። ይህ እርምጃ ተጠቃሚዎች የፈለጉትን የኤአይ ረዳት የመምረጥ ነፃነታቸውን ከማረጋገጡም በላይ በአንድ ድርጅት ላይ ብቻ ተገድበው እንዳይቆዩ ትልቅ ድጋፍ ያደርጋል።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *