G Tech Ethiopia – Blog

Intro to Edge TTS Converter

በተለያዩ አጋጣሚዎች ረጅም ጽሁፎችን ለማንበብ ጊዜ ሲያጥረን ወይም ለስራ እና ለትምህርት ጽሁፎችን ወደ ድምጽ መቀየር ሲያስፈልገን ተለዋዋጭ እና ፈጣን መተግበሪያ ማግኘት ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ብዙዎቹ መተግበሪያዎች የጽሁፉ መጠን ሲበዛ የማቋረጥ ባህሪ ይታይባቸዋል። ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና የንባብ ሂደታችንን ይበልጥ ቀለል ለማድረግ Edge_TTS_Converter የተባለ አዲስ መተግበሪያ ይዤላችሁ መጥቻለሁ።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

ይህ መተግበሪያ የ Microsoft neural voices ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማንኛውንም ጽሁፍ ልክ እንደ ሰው ድምጽ በሚሰማ እና ጥራቱ በተጠበቀ መልኩ ወደ ድምጽ ፋይል ይቀይራል።

የመተግበሪያው ዋነኛ ጥንካሬ እጅግ በጣም ረጅም የሆኑ ፋይሎችን ያለ ምንም እንከን እና መቆራረጥ ማስተናገድ መቻሉ ነው። ለዚህም እንዲረዳው parallel conversion የተባለ ዘዴን ይጠቀማል፤ ይህም ማለት ጽሁፉን በየክፍሉ ከፋፍሎ በአንድ ጊዜ ወደ ድምጽ ስለሚቀይረው የሚፈጀው ጊዜ በጣም አጭር ነው።

ለማሳያ ያህል፣ ከ115,000 በላይ Characters ያለውን ጽሁፍ በዚሁ መተግበሪያ ለመቀየር ሞክረን ነበር። ውጤቱም አስገራሚ ነበር፤ ከ3 ሰዓት በላይ የሚረዝም ጥራት ያለው የድምጽ ፋይል ምንም አይነት ስህተት ሳይታይበት ማዘጋጀት ተችሏል። በአማካይ አጠቃቀምም በሺዎች የሚቆጠሩ Characters ያላቸውን ሰነዶች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል። ይህም በተለይ ለጥናት፣ ለይዘት ፈጠራ (content creation) ወይም ጽሁፎችን ሰምቶ ለመረዳት ለሚመርጡ ሰዎች ትልቅ እገዛ ያደርጋል።

ሌላው የመተግበሪያው ልዩ ባህሪ ተደራሽነቱ ነው። ማንኛውም ሰው በተለይም ማየት የተሳናቸው ወገኖች ከ screen readers ጋር በቀላሉ እንዲጠቀሙት ተደርጎ የተሰራ ነው። እንደ Jenny እና Roger ያሉ ዘመናዊ ድምጾችን የሚጠቀም በመሆኑም የሚወጣው ድምጽ ግልጽ እና ለመስማት የማይሰለች ነው። በተጨማሪም የ Edge-TTS library ን በመጠቀም ከ cloud ጋር በቀጥታ ስለሚገናኝ፣ Microsoft የሚያቀርባቸውን ሁሉንም ቋንቋዎች ያለምንም ችግር መጠቀም ይቻላል።

ይህንን ጠቃሚ መተግበሪያ ሞክራችሁ የራሳችሁን አስተያየት ለመተግበሪያው ዲቨሎፐር እንድትሰጡ እጋብዛችኋለሁ።

ያላችሁን አስተያየት ለዲቨሎፐሩ በቴሌግራም ይላኩ

መተግበሪያውን ለማውረድ ከታች ያለውን ሊንክ መጠቀም ትችላላችሁ።

Download Edge TTS Converter

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

1
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *