G Tech Ethiopia – Blog

Intro to Tiera

Tiera ተጠቃሚዎች ያሉበትን ቦታ በትክክል እንዲረዱ እና የሚሄዱበትን አቅጣጫ በልበ ሙሉነት እንዲለዩ የሚያስችል በ AI የሚሰራ አዲስ Navigation App ነው። ይህ ነጻ መተግበሪያ በተለይ ማየት የተሳናቸው እና ዝቅተኛ እይታ ያላቸው ወገኖቻችንን የዕለት ተዕለት የጉዞ ተግዳሮቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት የተነደፈ ሲሆን፣ እጅግ ዝርዝር የሆኑ የ outdoor መመሪያዎችን ከግል ፍላጎት ጋር በሚጣጣም መልኩ ያቀርባል። በከተሞችም ሆነ በማያውቋቸው አዳዲስ አካባቢዎች አስተማማኝ መመሪያ በመስጠት ተጠቃሚው ያለ ስጋት እንዲንቀሳቀስ ያግዛል።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

ይህ መተግበሪያ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ መገኛ ቦታ የተለየ እና ጥንቃቄ የተሞላበት የ step-by-step መመሪያዎችን የሚሰጥ ሲሆን፣ አቅጣጫዎችን በ real-time የድምጽ መልዕክት ወይም በ audio እና vibration ምልክቶች ያሳውቃል። ተጠቃሚዎች የት ነኝ ወይም በዙሪያዬ ምን አለ የሚሉ ጥያቄዎችን ሲያነሱም መተግበሪያው ፈጣን ምላሽ ይሰጣል። ሌላው ልዩ የሚያደርገው ደግሞ የ Checkpoint ባህሪው ሲሆን፣ ይህም የስልኩን ካሜራ በመጠቀም ተጠቃሚው በትክክለኛው አቅጣጫ መጓዙን በተለይም መድረሻው ላይ ሲቃረብ እንዲያረጋግጥ ይረዳዋል።

Tiera የተጠቃሚውን የእርምጃ ፍጥነት እና የግል ምርጫዎችን መሰረት በማድረግ ራሱን የሚቀይር personalized navigation ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ለእግር ጉዞ የታለመ ቢሆንም በቅርቡ ለ public transport navigation ድጋፍ መስጠት ይጀምራል። ወደፊትም በትላልቅ መጓጓዣ ጣቢያዎች ውስጥ አቅጣጫን በቀላሉ ለመጠቆም እና የ transfers ሂደቶችን ለማሳለጥ የሚያስችሉ አዳዲስ ባህሪያትን ለማካተት በዝግጅት ላይ ነው።

መተግበሪያውን ለማግኘት፣ ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

አስተያየት ለአፑ ዲቨሎፐሮች ይላኩ

በመተግበሪያው ላይ የሚያጋጥም ችግር ካለ፣ እንዲጨመር የሚፈልጉት አገልግሎት ካለ ወይም ለማንኛውም አስተያየትና ድጋፍ፣ የሚከተለውን የኢሜል ሊንክ ይጠቀሙ

ኢሜል ይላኩ

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

1
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *