መግቢያ:
ይህ መተግበሪያ በኮምፒውተራችን ላይ የሚገኙና ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮችን ወይም ቫይረሶችን ፈልጎ ለማጥፋት የሚረዳ ነጻ አፕ ነው።
ኮምፒውተርዎ ላይ አስቀድሞ የሚገኝ ሲሆን፣ አጠቃቀሙም በጣም ቀላል ነው።
ለመጀመር የሚከተሉትን እርምጃዎች ይከተሉ፦
- በመጀመሪያ የኮምፒውተርዎ ኪቦርድ ላይ የሚገኘውን Windows ምልክት እና R ፊደልን በአንድ ላይ ይጫኑ።
- የሚመጣው ሳጥን ውስጥ
mrt
ብለው ይጻፉና Enterን ይጫኑ።
3. “ይህ መተግበሪያ ኮምፒውተርዎ ላይ ለውጥ እንዲያደርግ ይፈቅዳሉ?” የሚል ጥያቄ ሲመጣልዎ Yes (አዎ) የሚለውን ይምረጡ።
4. መተግበሪያው ሲከፈት Next የሚለውን ይጫኑ። በመቀጠል ሶስት አይነት አማራጮችን ያገኛሉ፦
ፈጣን ፍተሻ (Quick Scan)፦ ቫይረሶች በብዛት የሚደበቁባቸውን ቦታዎች ብቻ በፍጥነት ይፈትሻል።
ሙሉ ፍተሻ (Full Scan)፦ መላው የኮምፒውተርዎን ክፍል በጥንቃቄ ይፈትሻል። ይህ ብዙ ሰዓት ሊወስድ ይችላል።
የተመረጠ ፍተሻ (Customized Scan)፦ እርስዎ የፈለጉትን የተወሰነ ቦታ ብቻ እንዲፈትሽ ለማድረግ ነው።
ለጀማሪዎች ፈጣን ፍተሻ (Quick Scan) እንዲመርጡ ይመከራል። ምርጫዎን ከጨረሱ በኋላ Next የሚለውን ይጫኑ።
5. አሁን መተግበሪያው ኮምፒውተርዎን መፈተሽ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ ስንት ፋይሎች እንደተፈተሹና ቫይረስ ተገኝቶ እንደሆነ ማየት ይችላሉ።
ፍተሻው ሲያልቅ ውጤቱን ይነግርዎታል።
ምንም ቫይረስ ካልተገኘ Finish የሚለውን ተጭነው መዝጋት ይችላሉ።
ቫይረስ ከተገኘ ግን መተግበሪያው ራሱ እንዴት ማጥፋት እንደሚችሉ መመሪያ ይሰጥዎታል።
ጠቃሚ ማሳሰቢያ፦
ይህ መተግበሪያ በየወሩ ራሱን በራሱ ያድሳል። ነገር ግን ይህ አፕ በኮምፒውተርዎ ላይ ሁልጊዜ የሚቆይ ጥበቃ (Antivirus) ስላልሆነ፣ ሌላ መደበኛ የቫይረስ መከላከያ መኖሩን ማረጋገጥ አለብዎት።
Leave a Reply