ለአንድሮይድ ስልካችሁ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነ እና ለprivacy እጅግ ትኩረት የሰጠ አፕሊኬሽን ላስተዋውቃችሁ።
ToBe SAID: AI Voice & TTS የተባለው ይህ አፕ ሙሉ በሙሉ በስልካችሁ ላይ ብቻ (100% offline) የሚሰራ ጽሁፍን ወደ ድምጽ በመቀየር የሚያነብ ሲሆን ምንም አይነት ኢንተርኔት ሳይፈልግ ፅሁፎችን ወደ ተፈጥሯዊ የሰው ድምፅ ይቀይራል።
Follow us on Telegram
Join Our Telegram ChannelDownload ToBe SAID
ToBe SAIDን ፕለይ ስቶር ላይ ለማውረድ፣ ይህንን ይጫኑ።ይህ አፕ በዋናነት የሚለየው እንደ ሌሎቹ የ AI TTS መረጃችሁን ወደ ሰርቨር የማይልክ መሆኑ ነው። ማንኛውም የምታስነብቡት ፅሁፍም ሆነ የምትቀርጹት የራሳችሁ ድምፅ በስልካችሁ ውስጥ ብቻ ተቀምጦ ስለሚቀር ለደህንነታችሁ አስተማማኝ ያደርገዋል።
የ ToBe SAID አፕሊኬሽን እንደ System-Wide TTS engine ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ይህም ማለት አንድ ጊዜ በስልካችሁ ሴቲንግ ውስጥ ካስተካከላችሁት በኋላ ሌሎች እንደ TalkBack፣ eBook readers እና ሜሴጆችን እንዲያነብላችሁ ያደርጋል።
ከዚህ የበለጡ አገልግሎቶችን ለመጠቀም ToBe SAID Pro የሚባለውን የተከፈለበት ስሪት መጠቀም ትችላላችሁ። የ Pro ስሪቱ ዋጋው በ Google Play Store ላይ ዘጠኝ ዶላር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም አካባቢ ሲሆን ይህም አንድ ጊዜ የሚከፈል ክፍያ ነው።
የ Pro Subscription ወይም ክፍያውን መፈጸማችሁ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኝላችኋል ።
- Unlimited Custom Voice Slots: የፈለጋችሁትን ያህል የሰው ድምፆችን ቀርጻችሁ በአፕሊኬሽኑ ላይብረሪ ውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ። በነጻ የሚገኘው አፕሊኬሽን ላይ ግን የሚፈቀደው አንድ ብቻ ነው።
- System-Wide Personal Voice: የራሳችሁን ድምፅ ቀርጻችሁ ስልካችሁ ማንኛውንም መረጃ በናንተ ድምፅ እንዲያነብላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ።
- Faster Speech Generation: የድምፅ ማመንጨት ፍጥነቱ እጅግ ፈጣን ከመሆኑም በላይ የባትሪ አጠቃቀሙም የተሻለ ነው።
- Multi-language Support: በአሁኑ ወቅት ከእንግሊዝኛ በተጨማሪ እንደ ጣልያንኛ፣ ጀርመንኛ እና ፖርቹጋልኛ ያሉ ቋንቋዎችን ማንበብ ይችላል።።
ስለ መተግበሪያው ያላችሁን አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!
Leave a Reply