
CraftNote: ስብሰባዎችን እና ትምህርቶችን በ AI የሚዘግብላችሁ ድንቅ መተግበሪያ!
ሰላም የG Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ በተለይ ለተማሪዎች፣ ለባለሙያዎች እና በስብሰባ ብዛት ለሚወጠሩ ሰዎች እጅግ አስፈላጊ የሆነ አዲስ መተግበሪያ ይዘንላችሁ መጥተናል።
ስሙ CraftNote ይባላል። ይህ መተግበሪያ ተራ የድምጽ መቅጃ ሳይሆን፣ ንግግሮችን በቅጽበት ወደ ጽሁፍ የሚቀይር (Live Transcribe) እና በ AI አማካኝነት አጠር ያሉ ማጠቃለያዎችን (AI Summaries) የሚሰጥ ዘመናዊ የ AI Note Taker ነው።
Follow us on Telegram
Join our Telegram Channelክራፍት ኖትን ያውርዱ
ክራፍት ኖትን በፕለይ ስቶር ለማውረድ ይሄንን ይጫኑየ CraftNote ዋና ዋና Features
- Effortless AI Note-taking: ስብሰባዎችን፣ Lectures ወይም Voice Memos ስትቀዱ አፑ በራሱ ጊዜ ወሳኝ ነጥቦችን እየለየ ይመዘግባል።
- Live Transcription: ንግግሮችን በቅጽበት ወደ ጽሁፍ (Voice-to-text) የሚቀይር ሲሆን፣ በተለይ የተለያዩ ሰዎችን ድምጽ የመለየት (Multi-speaker detection) ብቃት አለው።
- AI-powered Summaries: ረጅም ሰዓት የወሰዱ ንግግሮችን አሳጥሮ ዋና ዋና ነጥቦችን፣ የተወሰኑ ውሳኔዎችን (Action items) እና Follow-ups በዝርዝር ያወጣልዎታል።
- Smart Organization: ማስታወሻዎችዎ በራሳቸው በ Tag እና በ Category ተከፋፍለው ስለሚቀመጡ በፈለጉት ጊዜ በቀላሉ Search አድርገው ማግኘት ይችላሉ።
- Cross-platform Sync: በማንኛውም Device ላይ ማስታወሻዎችዎን ማግኘት እንዲችሉ ከ Cloud ጋር በቀላሉ Sync ያደርጋል።
- Privacy & Security: መተግበሪያው የእርስዎ መረጃዎች በ Encryption ተቆልፈው በእርስዎ ቁጥጥር ስር ብቻ እንዲሆኑ ያደርጋል።
የ Free እና የ Pro version ንጽጽር
መተግበሪያውን በነጻ መጠቀም የሚቻል ቢሆንም፣ የ CraftNote Pro ስሪት ለየት ያሉ ጥቅሞችን ይዟል። ልዩነታቸውንም እንደሚከተለው ማየት ይቻላል.
- የ Transcription ደቂቃዎች ገደብ
- የ AI Summary ጥራት እና ጥልቀት
- የ Speaker Identification ብቃት
- Export and Sharing options
- Cloud Storage and Multi-Device Sync
በነጻው version በወር ውስጥ የምታገኙት የ Transcription ደቂቃ በጣም የተገደበ ነው። ይህ ማለት ጥቂት አጫጭር ስብሰባዎችን ወይም ማስታወሻዎችን ብቻ መቅዳት ትችላላችሁ።
የ Pro ቨርዥኑ ግን ያለ ምንም ገደብ ለፈለጋችሁት ያህል ሰዓት እንድትቀዱ እና ወደ ጽሁፍ እንድትቀይሩ ይፈቅድላችኋል። ይህ በተለይ በየቀኑ ስብሰባ ላለባቸው ባለሙያዎች ወሳኝ ነው።
ምንም እንኳ ሁለቱም versions AI Summary ቢሰጡም፣ የ Pro version የሚጠቀመው ይበልጥ የረቀቁ የ AI Models ነው።
በነጻው version አጠር ያለ እና አጠቃላይ የሆነ ማጠቃለያ ሲያገኙ፣ በ Pro version ግን ንግግሩን በዝርዝር የሚተነትን፣ ዋና ዋና ነጥቦችን በቅደም ተከተል የሚያስቀምጥ እና የተወሰኑ ውሳኔዎችን ለይቶ የሚያወጣ ጥልቅ ማጠቃለያ ያገኛሉ።
በስብሰባ መሃል ከአንድ በላይ ሰዎች ሲናገሩ ድምጹን ለይቶ የማወቅ ብቃት በ Pro version ላይ እጅግ የላቀ ነው።
ይህም በ Transcript ፋይሉ ላይ ማን ምን እንደተናገረ በስም ወይም በምልክት ለይቶ ስለሚያስቀምጥ፣ በኋላ ላይ ንግግሩን ለማንበብ በጣም ቀላል ያደርገዋል።
ማስታወሻዎችዎን ወደ ሌሎች መተግበሪያዎች ለመውሰድ ሲፈልጉ የ Pro version ሰፊ አማራጭ ይሰጥዎታል።
የ Free version ተጠቃሚዎች ማስታወሻውን ኮፒ በማድረግ ማጋራት ሲችሉ፣ የ Pro ተጠቃሚዎች ግን እንደ PDF, Microsoft Word, ወይም Markdown ባሉ ለስራ በሚመቹ Professional Formats Export ማድረግ ይችላሉ።
የ Pro version ሰፊ የ Cloud Storage ስለሚሰጥዎ፣ የፈለጉትን ያህል የድምጽ ፋይሎችን ማስቀመጥ ይችላሉ።
በተጨማሪም በስልክዎ የቀዱትን ማስታወሻ በታብሌት ወይም በኮምፒውተርዎ ላይ ያለምንም መቆራረጥ በ Real-time Sync እንዲያገኙ ያደርጋል።
CraftNote application ለስራዎ ምን ያህል ለውጥ ያመጣል ብለው ያስባሉ? ኮሜንት ሴክሽን ላይ ያጋሩን።
Leave a Reply