
ሰላም የቴክኖሎጂ ቤተሰቦች! ዛሬ በአንድሮይድ ስልካችሁ ላይ የሚዲያ ፋይሎችን ለማውረድ የምትጠቀሙበት እጅግ ገራሚ Open-source ሶፍትዌር ይዤላችሁ መጥቻለሁ።
ይህ አፕሊኬሽን YTDLnis የሚባል ሲሆን በ
Denis Cerriየሚመራ ፕሮጀክት ነው። በ
Githubላይ በነጻ የሚገኝ እና በየጊዜው በ Developer ኮሚዩኒቲው ማሻሻያ የሚደረግበት መተግበሪያ ነው።
Follow us on Telegram
Join our Telegram Channel
ለምን YTDLnis መጠቀም አለባችሁ?
ይህ አፕሊኬሽን የሚጠቀመው የዓለማችንን ቁጥር አንድ የሆነውን yt-dlp Engine በመሆኑ ከ
YouTube, SoundCloud, Instagramእና ከሌሎች 1,000+ Platforms ላይ በከፍተኛ ብቃት ሚዲያዎችን ማውረድ ይችላል።
እንደ GitHub ገለጻ አፑ በ Flutter የተገነባ በመሆኑ እጅግ ዘመናዊ እና Material UI Design ያለው User Interface አለው። ሌላው የዚህ ሶፍትዌር ልዩ ባህሪ የፋይሎችን Bitrates እና Codecs ሙሉ በሙሉ Control እንድታደርጉ መፍቀዱ ነው። በተለይ ለ Audio አፍቃሪያን ምንም አይነት Re-compression ሳያስፈልግ High-quality ፋይሎችን ቀጥታ Extract ለማድረግ ይመቻል።
መተግበሪያው ሙሉ በሙሉ Free እና Open-source ከመሆኑም በላይ ምንም አይነት የሚያበሳጩ Pop-up Ads ወይም Background Tracking የለበትም። ፋይሎችን በምታወርዱበት ወቅት High-res Thumbnails እና ID3 Tags በራሱ Embed ስለሚያደርግላችሁ የሚዲያ Library ለማደራጀት በጣም ቀላል ይሆንላችኋል።
ዋና ዋና Features:
- Multi-threading & Batch Download: ብዙ ፋይሎችን ወይም ሙሉ Playlist በአንድ ጊዜ ማውረድ ያስችላል።
- SponsorBlock Integration: በቪዲዮዎች ውስጥ ያሉትን አሰልቺ segments በራሱ Skip ያደርጋል።
- Video Cutting: ቪዲዮዎችን በ Timestamps ወይም በ Chapters መቁረጥ የሚያስችል Experimental feature አለው።
- Custom Commands: ለ advance users የራሳቸውን Custom yt-dlp commands እንዲጠቀሙ ይፈቅዳል።
- Cookies Support: በ Login የምታገኟቸውን Private ወይም Premium ቪዲዮዎች ለማውረድ ይረዳል።
- Live Notifications: በተለይ በ Android 16 ላይ አዳዲስ Live notification features አካቷል።
Download YTDLnis
ይህንን አፕሊኬሽን Playstore ላይ ማግኘት አትችሉም። ስለዚህ፣
Githubላይ ወይም የሚከተሉትን ሊንኮች በመጠቀም አፕሊኬሽኑን ከዚህ ዌብሳይት ማውረድ ትችላላቹህ።
Leave a Reply