G Tech Ethiopia – Blog

Mark Zuckerberg Is Building an AI Agent to Help Him Be CEO

የሜታ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ዙከርበርግ ተቋሙን በብቃት ለመምራት የሚያግዘውንና እጅግ የረቀቀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ወኪል በግሉ መጠቀም መጀመሩን አዳዲስ መረጃዎች አመለከቱ።
ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል በቅርቡ ባወጣው ዘገባ መሰረት ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ እንደ ተራ የኢሜይል ምላሽ ሰጪ ረዳት ሳይሆን በኩባንያው ውስጥ የሚገኙ ጥልቅ መረጃዎችን በቀጥታ ፈልጎ የማውጣት ልዩ አቅም ያለው ነው።

ዙከርበርግ ቀደም ሲል መረጃዎችን ለማግኘት በተለያዩ የስራ እርከኖች ውስጥ ማለፍና በርካታ ሰራተኞችን መጠየቅ ይጠበቅበት የነበረ ቢሆንም አዲሱ የኤአይ ወኪል ግን ከ78 ሺህ በላይ ሰራተኞች ባሉት የሜታ ኩባንያ ውስጥ ያለን ማንኛውንም መረጃ በቅጽበት እንዲያገኝ ያስችለዋል።
ይህ እርምጃ ሜታን ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚመራ ኩባንያ ለማድረግ ከታቀደው ሰፊ ስትራቴጂ አንዱ አካል መሆኑ ተገልጿል።
ኩባንያው ከዙከርበርግ የግል ረዳት በተጨማሪ ሰራተኞች የውስጥ ሰነዶችን በቀላሉ እንዲመረምሩ የሚያግዝ ሰከንድ ብሬን የተባለ ቴክኖሎጂ እና ሰራተኞች እርስ በእርስ መረጃ እንዲለዋወጡ የሚያግዙ ሌሎች የኤአይ መተግበሪያዎችን እያበለጸገ ይገኛል።
የዚህ ቴክኖሎጂ ዋና ግብ በኩባንያው ውስጥ ያለውን የቢሮክራሲ ሰንሰለት በማሳጠርና መዋቅራዊ መሰናክሎችን በማስወገድ ሜታ እንደ አንድ ግዙፍ ተቋም ሳይሆን እንደ አነስተኛና ፈጣን የቴክኖሎጂ ድርጅት እንዲንቀሳቀስ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ለውጥ በታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውስጥ ያለውን የአመራር ዘይቤ ሊቀይር የሚችል ትልቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *