G Tech Ethiopia – Blog

New update for Microsoft Excel march 2026

XL Logo

በመጋቢት 2026 የወጣው የExcel አዲስ ማስተካከያ በዋናነት በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በተጠቃሚዎች ምቾት ላይ ያተኮሩ በርካታ ማሻሻያዎችን ይዟል።

follow us on telegram

Join our Telegram Channel

ከእነዚህ መካከል ዋነኛው በ Work IQ የሚታገዘው አዲሱ የ Edit with Copilot አገልግሎት ነው። ይህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚዎች መረጃዎችን Manually መፈለግ ሳያስፈልጋቸው ሲስተሙ በራሱ ከኢሜይሎች፣ ከስብሰባዎች እና ከሌሎች ፋይሎች ተገቢውን መረጃ በመውሰድ ትክክለኛ ማስተካከያዎችን እንዲያደርግ ይረዳዋል።

ሌላው ትልቅ ዜና Claude Opus 4.6 የተባለው ሞዴል በኤክሴል ውስጥ እንዲካተት መደረጉ ነው። ይህ ሞዴል በተለይ ለM365 Premium ተጠቃሚዎች የሚቀርብ ሲሆን፣ በኤክሴል ውስጥ ያለውን አማራጭ በመጠቀም ስራ ላይ ሊውል ይችላል።

የ Office Scripts ተጠቃሚዎች ልምድንም ለማሻሻል የግራፊክስ UI ዳግም ተቀርጿል። አዲሱ ዲዛይን ተደጋጋሚ ስራዎችን ያለምንም የሰው ርዳታ የሚሰሩ ስክሪፕቶችን በቀላሉ ለመፍጠር፣ ለማስተዳደር እና ለሌሎች ለማጋራት እንዲመች ተደርጎ የተሰራ ነው።

በWeb ላይ የኤክሴል ፋይሎችን የመፈለግ ሂደትም ከበፊቱ በበለጠ ፈጣን ሆኗል። ተጠቃሚዎች የፋይሉን ስም በፍለጋ ሳጥኑ ውስጥ መጻፍ ሲጀምሩ፣ ሲስተሙ በራሱ ተዛማጅ ፋይሎችን ከስር በዝርዝር በማቅረብ ጊዜን ይቆጥባል።

የ Edit with Copilot አገልግሎት አሁን ላይ ሁሉንም የCopilot ቋንቋዎችን መደገፍ ጀምሯል። ይህም በተለያዩ ቋንቋዎች የሚሰሩ ተጠቃሚዎች የኤክሴል ሰንጠረዦችን በቀላሉ እንዲያቀናብሩ ይረዳቸዋል።

በተጨማሪም የኮፓይለት አገልግሎት በኮምፒውተራችን ላይ በተቀመጡ ፋይሎች ላይም እንዲሰራ ተደርጓል። ይህም መረጃዎችን ወደ Cloud ሳይሰቅሉ በቀጥታ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ትንታኔዎችን ለማግኘት ያስችላል።

ይህ አዲስ ማሻሻያ በተለይ ውስብስብ የሆኑ መረጃዎችን ለሚያስተዳድሩ እና የዕለት ተዕለት ስራቸውን ቀልጣፋ ለማድረግ ለሚፈልጉ ባለሙያዎች ትልቅ ፋይዳ አለው።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *