ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ዘንድ ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርጉትን በርካታ አዳዲስ ማሻሻያዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህ ወር ማሻሻያ ውስጥ የተካተቱት ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
Member Tags
በግሩፕ ውስጥ ያሉ አባላት በስማቸው አጠገብ የሚታይ አጭር ገላጭ ጽሁፍ ማከል ይችላሉ። ይህም በስራ ቦታ፣ በዩኒቨርሲቲ ወይም በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ አባላት ያላቸውን ሚና (ለምሳሌ፦ “Designer” ወይም “Student”) በቀላሉ ለመለየት ይረዳል። የግሩፕ አድሚኖች አባላት በራሳቸው ታግ እንዲጨምሩ መፍቀድ ወይም አድሚኑ ብቻ እንዲሰጥ ማድረግ ይችላሉ።
Disable Sharing in Private Chats (ለPremium ተጠቃሚዎች)
ይህ አዲስ ፊቸር ለTelegram Premium ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረበ ሲሆን፤ በማንኛውም የPrivate Chat ውስጥ ያሉ መልዕክቶችን ሌሎች ሰዎች Forward፣ ኮፒ እንዳያደርጉ ወይም የቪዲዮ እና የፎቶ Screenshot እንዳያነሱ ማገድ ያስችላል። ይህም የግል ቻቶችን ደህንነት ይበልጥ የተጠበቀ ያደርገዋል።
Login with Telegram
አሁን የተለያዩ ድረገጾችን ወይም አፕሊኬሽኖችን ሲጠቀሙ በቴሌግራም አካውንትዎ ብቻ Log In ማድረግ ይችላሉ። ይህ አሰራር አዳዲስ ፎርሞችን መሙላት ሳይጠበቅብዎት እና የግል ስልክ ቁጥርዎን ሳያጋሩ በቀላሉ አገልግሎቶችን ለማግኘት ይረዳል።
GIF and Sticker Editing
ተጠቃሚዎች ማንኛውንም GIF ወይም Sticker ከመላካቸው በፊት የቴሌግራምን Media Editor በመጠቀም ጽሁፍ፣ ስዕል ወይም ኢሞጂ ማከል ይችላሉ። በተጨማሪም የጂአይኤፎችን Trim ማድረግ ተችሏል።
Instant Photo Stickers
አሁን ማንኛውንም ፎቶ በአንድ ንክኪ ብቻ ወደ ስቲከር መቀየር ይቻላል። ቴሌግራም በፎቶው ላይ ያለውን ምስል ለይቶ በማውጣት በቀላሉ ስቲከር እንዲሆን ያደርገዋል፤ ተጠቃሚዎችም የፈለጉትን ጽሁፍ ጨምረው ወደ Favorites ማከል ይችላሉ።
Voting Timestamps
Voting Timestamps
Leave a Reply