ሰላም የ G Tech Ethiopia ቤተሰቦች! ዛሬ ደግሞ ስራ በሚበዛባቹህ ጊዜ፣ ከአሰልቺ ስብሰባዎች ወይም ካልተፈለጉ ንግግሮች በቀላሉ ለመውጣት የሚረዳችሁ ድንቅ መተግበሪያ ይዘንላችሁ መጥተናል።
መተግበሪያው Fake Call – Prank የሚባል ሲሆን፣ በ Play Store ላይ እጅግ ተወዳጅ ከሆኑት አንዱ ነው።
Follow us on Telegram
Join Our Telegram ChannelDownload Call – Prank
በፕለይስቶር ለማውረድ ይህንን ሊንክ ተጠቀሙ።ይህ App በተለይ ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች እንደ መውጫ መንገድ ሆኖ ያገለግላል። ለምሳሌ የማይመች ቀጠሮ ላይ ከሆናችሁ ወይም ከማይፈለግ ሰው ጋር እያወራችሁ ከሆነ፣ ስልካችሁ ላይ የውሸት ጥሪ እንዲመጣ በማድረግ በሰላም ለመሰናበት ትችላላችሁ። በተጨማሪም በጓደኞቻችሁ ላይ ቀልድ ለመቀለድ እጅግ በጣም አመቺ ነው።
የ Fake Call – Prank ዋና ዋና Features
- Customize Caller Info: የሚደውለውን ሰው ስም፣ ስልክ ቁጥር እና ፎቶ እንደ ፍላጎታችሁ መቀየር ትችላላችሁ።
- Schedule Calls: ጥሪው መቼ እንዲሆንላቹህ ጊዜ መወሰን ትችላላችሁ። ለምሳሌ ከ 10 ሰከንድ ወይም ከ 30 ሰከንድ በኋላ እንዲደወልላችሁ ማድረግ ይቻላል።
- Realistic Interface: የጥሪው ስክሪን (Call Screen) ልክ እንደ እውነተኛ ስልክ ጥሪ ሆኖ የተሰራ ነው፤ ጥሪውን ለመቀበል ወይም ለመዝጋት የሚያስችሉ Buttons አሉት።
- Voice Recording: ጥሪውን ስታነሱ የሚሰማ ድምፅ ቀድማችሁ መቅዳት ወይም በፋይል ውስጥ ያለ ድምፅ መምረጥ ትችላላችሁ። ይህም እውነተኛ ንግግር እያደረጋችሁ እንደሆነ ለማስመሰል ይረዳል።
- Offline Mode: መተግበሪያው ያለ ምንም የኢንተርኔት ግንኙነት የሚሰራ በመሆኑ በማንኛውም ቦታ ለመጠቀም ይመቻል።
ይህ መተግበሪያ ጥሪው እውነተኛ እንዲመስል የሚያደርጉ በርካታ Settings እና አማራጮችን አካቷል።
መተግበሪያውን እንዴት እንጠቀም?
መተግበሪያው እጅግ በጣም ቀላል የሆነ Interface ያለው ሲሆን አጠቃቀሙም እንደሚከተለው ነው።
- በመጀመሪያ
Simulate a Call
የሚለውን በመጫን የውሸት ጥሪውን ያስጀምሩ።። - የሚደውለውን ሰው ስም እና ቁጥር ያስገቡ፤ እንዲሁም የሚመችዎትን ፎቶ ይምረጡ።
- እንዲደወልልዎት የሚፈልጉትን ጊዜ ይወስኑ።
- በመጨረሻም
Schedule
የሚለውን በመጫን ጥሪውን ይጠብቁ።
ይህ መተግበሪያ በ Play Store ላይ ከ 75 ሚሊዮን በላይ ጊዜ Download የተደረገ ሲሆን፣ መተግበሪያውም ፕለይ ስቶር ላይ 4.54 stars አለው። መተግበሪያውን ለማውረድ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠይቅ ሲሆን፣ ትንሽ ማስታወቂያዎችን ሊያሳያችሁ ይችላል።
ስለ መተግበሪያው ያላችሁን አስተያየት በኮመንት መስጫው ላይ አጋሩን!
Leave a Reply