G Tech Ethiopia – Blog

Good news for Windows 11 users!

ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ 11 ተጠቃሚዎች አዳዲስ እና አጓጊ ማሻሻያዎችን ይፋ አደረገ
የMicrosoft Windows Devices ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት Pavan Davuluri ለዊንዶውስ ኢንሳይደር አባላት በላኩት ዝርዝር መልእክት መሰረት ኩባንያው የዊንዶውስ 11ን ጥራት ለማሳደግ እና የተጠቃሚዎችን ቅሬታ ለመፍታት ትልቅ እርምጃ እየወሰደ ነው። ቡድኑ ባለፉት ጥቂት ወራት የተጠቃሚዎችን አስተያየት በስፋት ሲያጠና የቆየ ሲሆን አሁን ላይ ተጨባጭ ለውጦችን ለማምጣት ቆርጦ ተነስቷል። ይህ ውሳኔ ዊንዶውስን በየቀኑ ለሚጠቀሙ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ትልቅ የምስራች ነው። በዚህም መሰረት ከዚህ ወር ጀምሮ እና በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ በርካታ መሰረታዊ ለውጦች በሙከራ ደረጃ ለተጠቃሚዎች ይቀርባሉ። እነዚህ ማሻሻያዎች የዊንዶውስን ፍጥነት፣ አስተማማኝነት እና አጠቃላይ የDesign ጥራት በእጅጉ እንደሚያሳድጉ ይጠበቃል።

Follow us on Telegram

Join our Telegram Channel

የታስክባር አቀማመጥ እና የኮፓይለት አጠቃቀም ማሻሻያ

ከብዙ ጊዜ ጥያቄ በኋላ ማይክሮሶፍት የታስክባር (Taskbar) አቀማመጥን የመቀየር ምርጫን ወደ ዊንዶውስ 11 መልሶ እያመጣ ነው። ተጠቃሚዎች አሁን ታስክባሩን ከስክሪናቸው አናት ላይ ወይም በጎን በኩል ማስተካከል የሚቻልበትን መንገድ ማይክሮሶፍት እያመቻቸ ነው።

በሌላ በኩል ማይክሮሶፍት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም AI Copilot በዊንዶውስ ውስጥ የሚያዋህድበትን መንገድ እያሻሻለ ነው። ኮፓይለት እጅግ ጠቃሚ በሆኑ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲገኝ በማድረግ አላስፈላጊ የሆኑ Integrations እየቀነሰ ይገኛል። ለምሳሌ Snipping Tool, በPhotos፣ በwidgets እና በNotepad መተግበሪያዎች ላይ የነበረው የኮፓይለት ትስስር ይቀነሳል። ይህ እርምጃ ቴክኖሎጂው የተጠቃሚዎችን ስራ ከማወሳሰብ ይልቅ ይበልጥ አጋዥ እና ግልጽ እንዲሆን ያለመ ነው።

የፋይል ኤክስፕሎረር አዲስ ለውጥ እና የዊንዶውስ አፕዴት ቁጥጥር

በዊንዶውስ ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ ከሚውሉት መተግበሪያዎች አንዱ የሆነው File Explorer ከፍተኛ ማሻሻያ እየተደረገለት ነው።

አዲሱ ማሻሻያ መተግበሪያው በፍጥነት እንዲከፍት፣ የፋይል ፍለጋን እጅግ ፈጣን እንዲያደርግ ተደርጎ እየተሰራ ነው። ትላልቅ ፋይሎችን ኮፒ ማድረግ እና ማንቀሳቀስም ይበልጥ አስተማማኝ እና ፈጣን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ, Windows Update አሰራር ላይ ትልቅ የተጠቃሚ ነጻነት ተሰጥቷል። በዚህ እቅድ መሰረት፣ ተጠቃሚዎች አፕዴቶችን በሚፈልጉት ጊዜ ማቆም፣ ኮምፒውተራቸውን ሲያበሩ አፕዴት እንዳይደረግ መከልከል፣ እንዲሁም ኮምፒውተራቸውን ሲያጠፉ ወይም ሪስታርት ሲያደርጉ ያለ አፕዴት ማስጀመር እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህም አላስፈላጊ የሆኑ የሪስታርት መልእክቶችን እና የስራ መስተጓጎልን በእጅጉ እንደሚቀንስ ታምኖበታል።

ግልጽ እቅዶች

ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 11ን አጠቃላይ አፈጻጸም ይበልጥ ፈጣን እና ምቹ ለማድረግ ሰፋ ያለ እቅድ አውጥቷል።

የSystem resource usage በመቀነስ ተጨማሪ ሜሞሪ ለሌሎች መተግበሪያዎች ክፍት እንዲሆን ይደረጋል።

የዊንዶውስ መሰረታዊ ክፍሎችን ወደ WinUI3 ማዕቀፍ በማሸጋገር የመተግበሪያዎች ምላሽ ሰጪነት እና የስታርት ሜኑ ፍጥነት ይጨምራል።

ለሶፍትዌር ዲቨሎፐሮችም WSL የፋይል አጠቃቀም እና የኔትወርክ ፍጥነት እንደሚሻሻል ማይክሮሶፍት ቃል ገብቷል።

የብሉቱዝ ግንኙነቶችን ማጠናከር፣ የዩኤስቢ እና የካሜራ ግንኙነት መቆራረጥን ማስቀረት እንዲሁም የዊንዶውስ ሄሎ (Windows Hello) የፊት እና የጣት አሻራ ማረጋገጫዎችን ይበልጥ ትክክለኛ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማድረግ የዚህ ትልቅ እቅድ አካል ናቸው።

የተሻሻለ የተጠቃሚ ተሞክሮ እና የዊንዶውስ ኢንሳይደር ፕሮግራም

Widgets ትኩረትን ከሚከፋፍሉ ይልቅ ይበልጥ ጠቃሚ እና ተገቢ እንዲሆኑ ተደርገው እየተሻሻሉ ነው። ተጠቃሚዎች ዊጄቶች መቼ እና እንዴት እንደሚታዩ የተሻለ ቁጥጥር ይኖራቸዋል።

በተጨማሪም የዊንዶውስ ኢንሳይደር ፕሮግራምን እና Feedback Hub መተግበሪያን በማደስ ተጠቃሚዎች አስተያየታቸውን በቀላሉ እንዲያካፍሉ እና የዊንዶውስን የወደፊት እጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

በአጠቃላይ ይህ የማሻሻያ ርምጃ ማይክሮሶፍት የተጠቃሚዎችን ድምጽ በትኩረት እየሰማ መሆኑን እና ዊንዶውስ 11ን ለሁሉም ሰው የተሻለ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ያሳያል።

ይመዝገቡ!

በየጊዜው የምናጋራውን የቴክ መረጃ ቀድሞ እንዲደርስዎ ይፈልጋሉ?

መልስዎ “አዎ” ከሆነ፣ ቀጥሎ ያሉትን መጠይቆች በጥንቃቄ ይሙሉና የ G Tech Ethiopia ቤተሰብ ይሁኑ.

ከተመዘገቡ በኋላ የሚያመልጥዎ አንድም ነገር አይኖርም!

0
0

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *